Tuesday, December 22, 2020

የዕለተ ማክሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

 

እንግሊዛዊው የማንቸስተር ሲቲ ተከላካይ ጆን ስቶንስ ለተጨማሪ አመታት በኤቲሀድ ለመቆየት አዲስ ኮንትራት ሊፈርም ነው።ፔፕ ጓርዲዮላ በዘንድሮው አመት ከወትሮው ደካማ ቡድን መስራቱ ይታወቃል።

(Telegraph - subscription required)






ሙሐመድ ሳላህ ምንም እንኳን በአንፊልድ ደስተኛ ባይሆንም ሊቨርፑል ግን ለመሸጥ እንደማይፈልግ ሰን አስነብቧል።

(Sun)






ኦስትሪያዊው የግራ መስመር ተከላካይ ዳቪድ አላባ ባየርን ሙኒክ ያቀረበለትን የውል ማራዘሚያ ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።ቼልሲ ፣ ሪያል ማድሪድ እና ፓሪሰን ዤርመን የተጨዋቹ ፈላጊዎች ናቸው።

(Mail)






አርሰናል ዩራጓዊውን የቫሌንሲያ አጥቂ ማክሲ ጎሜዝ ከቫሌንሽያ ለማዘዋወር እየሰራ መሆኑን ሚረር አስነብቧል።

(Mirror)






ኤቨርተን ለፈረንሳዊው የግራ መስመር ተከላካይ ሉካስ ዲኜ አዲስ ኮንትራት አቅርቧል።ማንቸስተር ሲቲ ከተጫዋቾቹ ፈላጊዎች መሀከል ነው።

(Times - subscription required)






ፓሪሰን ዤርመን በበርካታ ክለቦች በጥብቅ የሚፈለገውን ስሎቬኒያዊውን የአትሌቲኮ ማድሪድ  ግብ ጠባቂ ያን ኦብላክ ለማዘዋወር እየሞከረ ይገኛል።

(Mail)






ማንቸስተር ዩናይትድ ኢኮዶሯዊውን አማካይ ሞይሰስ ካይሴዶ ለማዘዋወር በመስራት ላይ ነው።ተጨዋቹ በኢንዲፔንደንቴ በመጫወት ላይ ይገኛል።

(Manchester Evening News)






የሪያል ማድሪዱ ፕሬዝዳንት ፍሎረንቲኖ ፒሬዝ በኮቪድ ምክንያት የተቀየረው የሻምፒዮንስ ሊግ ፎርማት ድጋሚ መታየት አለበት ብለዋል።

(Independent)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...