Thursday, December 31, 2020

የዕለተ ሐሙስ ስፖርታዊ ዜናዎች

          አዘጋጅ - ኢብራሂም ሙሐመድ 




 ማንችስተር ሲቲዎች በዚህ አመት ከባርሴሎና ጋር ኮንትራቱ የሚጠናቀቀውን ሊዮኔል ሜሲን እንደሚያስፈርሙት መተማመናቸውን Daily Telegraph አስነብቧል።ከማንችስተር ሲቲ በተጨማሪ ፒኤስጂ ሜሲን ለማስፈረም ትልቅ እድል ያለው ክለብ ነው። 





ኤሲሚላኖች አይቮሪኮስታዊውን የክርስቲያል ፓላስ የመስመር አጥቂ ዊልፍሬድ ዘሀን በጥር የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው Mirror አስነብቧል። ዘሀን ከኤሲ ሚላን በተጨማሪ ፖቸቲኖን ለመቅጠር ከጫፍ የደረሱት ፒኤስጂዎችም ይፈልጉታል። 





ማንችስተር ዩናይትዶች በዚህ አመት ኮንትራቱ ለሚጠናቀቀው የቀኝ መስመር ተከላካይ ፎሱ ሜንሳህ ተጨማሪ የ3 አመት ኮንትራት እንዳቀረቡለት M.E.N አስነብቧል። እንደ Football Insider ዘገባ ደሞ ተጨዋቹ በጥር ዩናይትድን መልቀቅ ይፈልጋል ።ልጁንም ለማስፈረም ማርሴይ እና ሄርታ በርሊን ይፈልጉታል። 





ጄኑዋዎች የላዚዮውን የ24 አመት ተከላካይ ዴኒስ ቫርቮን ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸውን ታማኙ Gianluca Di Marzio ዘግቧል። ጄኑዋ ለተከላካዩ እስከ €15m እንደሚያወጡ ሲታወቅ በቀጣይ ሳምንት የህክምና ምርመራውን አድርጎ በይፋ ጄንዋን እንደሚቀላቀል ታውቋል። 





ቫንዳይክን ለረጅም ወራት ከሜዳ ያጡት ሊቨርፑሎች ተከላካይ ፍለጋቸውን አሁንም ቀጥለውበታል አሁን ደግሞ ፊታቸውን የኢንተር ሚላን ክሮሺያዊ ተከላካይ ሚላን ስክሪናር ላይ ማዞራቸውን Calcio Mercato አስነብቧል። ኢንተር ሚላኖች ለተጨዋቹ በቂ ገንዘብ ከቀረበ ለመልቀቅ ዝግጁ መሆናቸው ተሰምቷል። 





ጁቬንቱሶች በድጋሚ የፈርናንዶ ሊዮሬንቴ ፈላጊ ሆነው ብቅ ብለዋል።በናፖሊ የመሰለፍ እድል እያገኘ የማይገኘው ሊዮሬንቴ ናፖሊን ለመልቀቅ ይፈልጋል።ይህን ተከትሎ ጁቬዎች ልጁን ለመውሰድ ፍላጎት እንዳላቸው Tuttosport አስነብቧል። 





ማንችስተር ዩናይትዶች የአሮዋን ቢሳካ ተፎካካሪ ለማድረግ የኖርዊቹን የቀኝ መስመር ተከላካይ ማክስ አሮንስን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው Daily Express አስነብቧል። ባሳለፍነው ክረምት የዝውውር መስኮት አርሰናል እና ቶተንሀም ልጁን ለማስፈረም ጥያቄ አቅርበው ውድቅ እንደተደረገባቸው የሚታወስ ነው። 





አርሰናሎች በድጋሚ ዴንማርካዊው የኢንተር ሚላን አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን ላይ ፍላጎት አሳይተዋል። ተጨዋቹ በስፋት ስሙ ከፒኤስጂ ጋር እየተነሳ ቢገኝም መድፈኞቹ ልጁ ላይ ትልቅ ፍላጎት እንዳላቸው Gazzetta Dello Sport አስነብቧል። መድፈኞቹ ከኤሪክሰን በተጨማሪ የማድሪዱ ኢስኮ ላይም ፍላጎት አላቸው። 




ናፖሊዎች ጣሊያናዊውን የቸልሲ የግራ መስመር ተከላካይ ኤመርሰንን ለመውሰድ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን Corriere Dello Sport አስነብቧል። ኤመርሰን በቸልሲ ሶስተኛ ተመራጭ ሲሆን ቸልሲንም መልቀቅ እንደሚፈልግ ታውቋል። 





ባርሴሎና፣ሪያል ማድሪድ እና ሲቪያ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር በስምምነት ለመለያየት ከጫፍ የደረሰውን ዲያጎ ኮስታን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው SPORT አስነብቧል። ተጨዋቹ በእንግሊዞቹ አርሰናል ፣ ወልቭስ እና ቶተንሀምም እንደሚፈለግ ዴይሊ ሜይል አስነብቧል። 





በዚዳን ስር የመሰለፍ እድል እያገኘ የማይገኘው ስፔናዊው አማካይ ኢስኮ ከበርናባው ለመልቀቅ ፍላጎት እንዳለው እና ይፋዊ የልቀቁኝ ጥያቄ ለማቅረብ እንደተዘጋጀ ማርካ አስነብቧል። ተጨዋቹን አርሰናል እና ሲቪያ በውሰት ለማስፈረም ፍላጎት ቢያሳዩም ዚዳን ልጁን ለመልቀቅ አይፈልግም። ነገር ግን ማድሪዶች ልጁን ሚለቁት ከሆነ እስከ £20m ይፈልጋሉ።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...