Sunday, December 27, 2020

ክርስቲያኖ ሮናልዶ !






 ከእያንዳንዱ ስኬታማ ሰው ዛሬ ጀርባ በርካታ ከባድ እና አታካች ትናንቶች

አልፈዋል።
አስተዳደጉ በፈተናዎች የተሞላ ነበር።ምግብ ከበርገር ቤት ለምኖ ከጓደኞቹ ጋር
የተመገበባቸው ቀናት እልፍ ነበሩ።በአስራዎቹ አጋማሽ ሳለም ከባድ የልብ
ህመም አጋጥሞት 'ከዚህ በኋላ እግር ኳስን እርም በል' ቢባልም በእናቱ አጋዥነት
ከቀዶ ጥገና በኋላ በርትቶ በመስራት አሁን ያለበት ደረጃ ደርሷል።ታዳጊ ሳለ
ለጓደኞቹ 'አንድ ቀን የዓለማችን ምርጡ ተጨዋች እሆናለሁ' ሲላቸው
አፊዘውበታል ፥ አሁን በዚህ ሀሳብ የሚስማሙ ሚሊየኖች ናቸው።
ይህ አሁን በሰውነቱ ቅርጽ ብዙዎች የሚደመሙበት ሰው በታዳጊነቱ ጓደኞቹ
በቀጫጫነቱ የሚሳለቁበት ሰው ነበር።
አሁን ይህ ሰው በግሉም ፣ ከክለብ ጋር እንዲሁም ከሀገሩ ጋር ስሙን በወርቅ
ብዕር ጽፏል።የአምስት ባሎንዶሮች እንዲሁም የእልፍ አዕላፍ ስኬቶች ባለቤት
ነው።አለም ላይ እግርህ እስኪኳትን ብትዞር 'ክርስቲያኖ ሮናልዶ' የሚለው ስም
የማይታወቅበት ሀገር ልታገኝ አትችልም


No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...