አዘጋጅ - ኢብራሂም ሙሐመድ
ማንችስተር ዩናይትድ ብዙ ፈላጊ ያለውን የሌንስ ተከላካይ ፋኩንዶ ሜንዲን የማስፈረም ፍላጎት አለው። ሜንዲ የዩናይትድ ዋነኛው ተፈላጊ አይደለም ነገር ግን ማስፈረም የሚፈልጓቸው ተጨዋቾች ዝርዝር ውስጥ አለ ፤ የተጨበጠ ነገር ግን የለም።
ብራይተኖች አዲሱ የዲቮክ ኦሪጊ ፈላጊ ሆነው ብቅ ብለዋል።ተጨዋቹ በጥር የዝውውር መስኮት ከአንፊልዱ ክለብ ለመልቀቅ መዘጋጀቱን Eurosport አስነብቧል። ኦሪጊ ከብራይተን በተጨማሪ ሊድስ ፣ፊዮረንቲና እና ሻልክ04 ይፈልጉታል።
ከሪያልማድሪድ ጋር ኮንትራቱ በዚህ አመት ሚጠናቀቀው ሉካ ሞድሪች በበርናባው ተጨማሪ አመት ለመቆየት ከስምምነት መድረሱት ማርካ አስነብቧል።በሪያል ማድሪድም እስከ 2022 የሚያቆየውን አዲስ ውል በዚህ ሳምንት እንደሚፈርም ታውቋል።
ፒኤስጂዎች በጥር የዝውውር መስኮት ኢንተር ሚላንን እንደሚለቅ እርግጥ የሆነውን ኤሪክሰንን ለመውሰድ ለኢንተሮች ሊኦናርዶ ፓራዴዝን ለመስጠት እንደሚፈልጉ Le10Sport አስነብቧል።ይህንንም ጥያቄ ኢንተሮች ላይቀበሉት ይችላሉ ፤ ምክንያቱም ኢንተሮች ኤሪክሰንን በሽያጭ ብቻ ነው መልቀቅ ሚፈልጉት።
ሻልክ 04 ቱርካዊውን ተከላካይ ኦዛን ካባክን በጥር ለመልቀቅ እንደሚፈልጉ የጀርመኑ ቢልድ አስነብቧል።ሻልኮች ልጁን ለማቆየት ፍላጎት የነበራቸው ቢሆንም በክለቡ ውጤት ካባክ ደስተኛ አይደለም።ይህንንም ተከትሎ ልጁን ለመልቀቅ ተገደዋል። ልጁን ለማስፈረም ሊቨርፑል እና ዩናይትድ ተፋጠዋል።
ሪያል ማድሪድ እና ማንችስተር ዩናይትድ የባየርን ሙኒኩን የዳቪድ አላባን ፊርማ ለማግኘት ተፋጠዋል። በሙኒክ ኮንትራቱን እንደማያራዝም የተረጋገጠው አላባ ወደ አንዳቸው መሄዱ እርግጥ ይመስላል።ነገር ግን እሱ የጠየቀውን ሳምንታዊ ደሞዙን ከማንችስተር ዩናይትድ ይልቅ ሪያል ማድሪድ ለመክፈል ፍላጎት እንዳላቸው ማርካ አስነብቧል።
ጁቬንቱሶች የቀድሞ ልጃቸውን ፖል ፖግባን ከማንችስተር ዩናይትድ ለማስፈረም ከመቼውም ጊዜ በላይ ፍላጎት ማሳየታቸውን Calcio Mercato አስነብቧል። ጁቬዎች በጥር ፖግባን በውሰት ወስደው በቀጣይ ክረምት ዝውውሩን ቋሚም ለማረግ ሀሳብ እንዳላቸው ታውቋል።
ሪያልማድሪዶች በግራ መስመር ተከላካይ የማርሴሎ የረጅም ጊዜ ተተኪ ለማድረግ የስፖርቲንግ ሊዝበኑን ኑኖ ሜንዴዝን ለማስፈረም እንቅስቃሴ መጀመራቸውን Mundo Deportivo አስነብቧል።
No comments:
Post a Comment