Monday, December 28, 2020

የዕለተ ሰኞ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ስፖርታዊ ዜናዎች

           አዘጋጅ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)

የሀገር ውስጥ 

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰበታ ከነማን 4ለ2 በሆነ ውጤት አሸንፏል።ፈረሰኞቹ ዛሬ ሶስተኛ ተከታታይ ድላቸውን ነው ያስመዘገቡት።






ከውጭ

አርሰናል ጀርመናዊውን አማካይ ሜሱት ኦዚል በውሰት ወደ ዩቬንትስ ለስድስት ወር ለመስጠት ጥያቄ አቅርቧል።መድፈኞቹ እየተጫወተ ያልሆነውን አማካይ በመሸኘት ለተጨዋቹ የሚከፍሉትን ከፍተኛ ገንዘብ መቀነስ ይችላሉ።

(Tuttosport via Sun)






ማንቸስተር ዩናይትድ ኦስትሪያዊውን የግራ መስመር ተከላካይ ዳቪድ አላባ ለማዘዋወር የሚያደርገውን ጥረት ቀጥሏል።ሆኖም ቀያይ ሰይጣኖቹ በባየርን ሙኒክ እየቀረበ ባለው የዝውውር ገንዘብ ውድ ነው ብለው ስለሚያምኑ ደስተኞች አይደሉም።

(The Athletic)






አርሰናል ከማንቸስተር ሲቲን እና ባየርን ሙኒክ የተሻለ ገንዘብ በማቅረብ  የብራይተኑን የቀኝ መስመር ተከላካይ ታሪቅ ላምፕቴይ ለማዘዋወር እየሞከረ ነው።ሄክቶር ቤሌሪን ወደ አሳዳጊ ክለቡ ባርሴሎና እንደሚመለስም ይጠበቃል።

(Mirror)







የቀድሞው የቶተንሀም አሰልጣኝ ማውሩሲዮ ፖቼቲንሆ ፓሪሰን ዤርመንን ለማሰልጠን ተስማምቷል።የፓሪሱ ክለብ ላሰናበተው አሰልጣኙ ቶማስ ቱሀልም ካሳ £5.4ሚ. ከፍሏል።

(Fabrizio Romano via Sun)







ዎልቭስ የሪያል ማድሪዱን ሰርቢያዊ አጥቂ ሉካ ዮቪች በውሰት ለማዘዋወር እየሰራ ነው።

(The Athletic - subscription required)







እንግሊዛዊው አማካይ ፊል ፎደን በቋሚነት የመጫወት ዕድል ባለማግኘቱ ምክንያት ከክለቡ የመልቀቅ ፍላጎት አለው።

(Telegraph - subscription required)







ቶተንሀም በኢንተር ሚላን የሚገኘውን የቀድሞው ተጫዋቹን ክርስቲያን ኤሪክሰን በድጋሚ ለማዘዋወር እየሞከረ ነው።ዴንማርካዊው አማካይ በጣሊያን እንደተጠበቀው አልሆነም።

(Calciomercato - in Italian)






ኔዘርላንዳዊው የ30 አመት አማካይ ጆርጂንሆ ዋይናልደም በሊቨርፑል ለተጨማሪ አመታት የሚያቆየውን ኮንትራት ከሰሞኑ የሚፈርም ይሆናል።

(Guardian)






No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...