Thursday, October 8, 2020

የዕለተ ሐሙስ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

 በክረምቱ የሩበን ዲያዝ እና የናታን አኬ ኢትሀድ መድረስን ተከትሎ የመሰለፍ እድል እንደማያገኝ ያወቀው ጆን ስቶንስ ኢትሀድን መልቀቅ ይፈልጋል። ይህን ተከትሎ ቶተንሀሞች ስቶንስን መውሰድ ይፈልጋሉ። ቶተንሀሞች ለሲቲ ያቀረቡት የመጀመሪያ የውሰት ጥያቄም ውድቅ ተደርጎባቸዋል። 






ማንችስተር ዩናይትዶች ከፈረንጆች አዲስ አመት በፊት አሰልጣኙን ሶልሻየርን ለማሰናበት ፍላጎት እንዳላቸው ተሰምቷል። ከታክቲክ ጋር ችግር ያለበት ኦሌን እስከ ታህሳስ ድረስ  ጊዜ ሰተውታል። በተጨማሪም ቦርዱ ቀጣይ አሰልጣኝ ፖቸቲንሆ እንዲሆን ንግግር ሳይጀምሩ እንዳልቀረ ESPN አስነብቧል። 





በዝውውሩ መዝጊያ ላይ ሎፍተስ ቺክን ለፉልሀም በውሰት አሳልፈው የሰጡት ቸልሲዎች ተጨማሪ ወጣት ተጨዋቾችን ወደ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በውሰት ለመስጠት ይፈልጋሉ። በተጨማሪም ላምፓርድ ዴክላን ራይስንም ወደ ብሪጅ ለማምጣት ይፈልጋሉ። 






በዚህ የዝውውር መስኮት ወደ ባርሴሎና ለመሄድ እጅጉን ፈልጎ የነበረው ኤሪክ ጋርሺያ ወደ ባርሳ አለመሄዱ እጅጉኑ አስቆጭቶታል።ሆኖም ጋርሲያ በጥር የዝውውር መስኮት ወደ ባርሴሎና በነፃ መዘዋወር እንደሚፈልግ ነግሮዋቸዋል። 






ማንችስተር ዩናይትዶች በክረምቱ በስፋት ከጃደን ሳንቾ ጋር ሲነሳ ቆይቷል ፥ ዝውውሩ ሳይሳካ ቢቀርም ይህንን ተከትሎ ዩናይትዶች ሳንቾን በጥር የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ጥረት እንደሚያደርጉ MEN አስነብቧል። 






ሰርጂዮ ሮሜሮን ከዩናይትድ ያስፈርማሉ ተብለው ሲጠበቁ የነበሩት ኤቨርተኖች በመጨረሻ ሰአት የሮማውን ሮቢን ኦልሰንን በውሰት አስፈርመውታል። ግብ ጠባቂው ባሳለፍነው ሲዝን በሴሪያው በካግሊያሪ በውሰት አሳልፎ ነበር። 






የቀድሞ የአርሰናል ኮከቦች ጃግ ዊልሼር እና ዳኒ ዊልቤክ ከክለቦቻቸው ጋር በጋራ ስምምነት ተለያይተዋል። ዊልሼር በጉዳት ምክንያት እንደተጠበቀው ዌስትሀምን ማገልገል አልቻለም። ይሄንን ተከትሎ በስምምነት ለቀውታል። ዊልቤክም አንድ አመት ኮንትራት እየቀረው በስምምነት ተለያይቷል። ሁለቱም ተጨዋቾች በዚህ ሰአት ከኮንትራት ነፃ ሆነዋል። 






ቶተንሀም እና ዌስትሀም ዩናይትድ በዌልሳዊው የስዋንሲ ተከላካይ በ22 አመቱ  ጆ ሮንዶን ዝውውር ላይ ተፋጠዋል።ለቀጣዩ የዝውውር መስኮት ሳይዘጋ ተጨዋቹን ለመውሰድ ሁለቱም ክለቦች ለስዋንሲ ጥያቄ ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...