Monday, October 5, 2020

የዕለተ ሰኞ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች


 

በሚኬል አርቴታ እንደማይፈለግ የተነገረው ማቲዮ ጊውንዶዚ ወደ ቡንደስሊጋው ክለብ ሀርታ በርሊን የሚያደርገው ዝውውር ዛሬ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።

(Mirror)






የጆዜ ሞሪንሆው ቶተንሃም ዛሬ ምሽት የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት የኢንተር ሚላኑን ስሎቫኪያዊ ተከላካይ ሚሊያን ስክሪኒያር ለማዘዋወር እየሰራ ነው።

(Mirror)






የባርሴሎናው አሰልጣኝ ሮናልድ ኪውመን ፈረንሳዊው አጥቂ ኦስማን ዴምቤሌ በካምፕ ኑ እንዲቆይ እንደሚፈልጉ አሳውቀዋል።ዴምቤሌ ስሙ ከማን ዩናይትድ ጋር በስፋት ሲያያዝ መቆየቱ ይታወሳል።

(Evening Standard)






ኔዘርላንዳዊው አጥቂ ሜንፊስ ዴፓይ ባርሴሎናን ከመቀላቀል በግሉ ከስምምነት ላይ ደርሷል።ዝውውሩ ዛሬ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።

(Telefoot via Goal)






ዩቬንትስ ጣሊያናዊውን የግራ መስመር ተከላካይ ኤመርሰን ፓልሜሪ ከቼልሲ በውሰት ለመውሰድ ጥያቄ አቅርቧል።

(Calciomercato - in Italian)






አርሰናል የጋናዊውን አማካይ ቶማስ ፓርቴይ የውል ማፍረሻ £45ሚ. ለአትሌቲኮ ማድሪድ ለመክፈል ፈቃደኛ አይደለም።

(Mirror)







ሳውዝሀምተን እንግሊዛዊውን የቀኝ መስመር ተከላካይ ብራንደን ዊልያምስ በውሰት ከማን ዩናይትድ ለመውሰድ ጥያቄ አቅርቧል።

(Telegraph - subscription required)






ጂየን ክሊየር ቶዲቦ በውሰት ባርሴሎናን ለቅቆ ኤቨርተንን አሊያም ፉልሀምን በዛሬው ዕለት እንደሚቀላቀል ይጠበቃል።

 (Le 10 Sport - in French)






ባየርን ሚውኒክ ሀዲሰን ኦዴዬን ከቼልሲ ለማዘዋወር የሚያደርገው ጥረት ባለመስመሩ አይኑን በድጋሚ ወደ ብራዚላዊው የዩቬንትስ የመስመር አጥቂ ዳክላስ ኮስታ አዙሯል።

(Kicker - in German)






በቼልሲ የሁለት አመት ውል ይቀረው የነበረው ጀርመናዊው ተከላካይ አንቶኒ ሩዲገር ኤሲ ሚላንን ለመቀላቀል ከስምምነት ላይ ደርሷል።

(90min)






ፓሪሰን ዤርመን ፖርቱጋላዊውን የፖርቶ የተከላካይ አማካይ ዳኒሎ ፔሬራ በውሰት ለመውሰድ ጥያቄ አቅርቧል።

(Goal)






ፓሪሰን ዤርመንን የለቀቀው ካሜሮናዊው አጥቂ ኤሪክ ቹፖሞቲንግ በባየርን ሚውንክ የሁለት አመት ውል ኮንትራት ፈርሟል።

(Kicker - in German)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...