የማርሴሎ ቤልሳው ሊድስ ዩናይትዶች በሚቀጥሉት 48ሰአታት ውስጥ ሁለት ዝውውሮች ለማጠናቀቅ እየሰሩ ይገኛሉ። ሊድሶች የመጀመሪያ ፍላጎታቸው የኖርዊች ሲቲው ካንትዌል ሲሆን ለልጁ የተሻሻለ ሂሳብ እንዳቀረቡ ተሰምቷል። በተጨማሪም የዩናይትዱን ዳንኤል ጀምስን በመጨረሻ ሰአት ሊያስፈርሙ ፍላጎት አላቸው።
ሊዮኖች ተጨዋቾቻውን በክረምት የዝውውር መስኮት እንደማይለቁ ፕሬዝዳንቱ ዛሬ ይፋ አድርገዋል። አርሰናሎች አዋርን ለማስፈረም ድርድር ላይ የነበሩ ቢሆንም በስተመጨረሻ ንግግሩ ተቋርጧል።በተጨማሪም ዴፓይም ወደ ባርሴሎና ያመራል ቢባልም በስተመጨረሻ ሊዮንን ሳይለቅ ቀርቷል።
ማንችስተር ዩናይትዶች በመጨረሻ ሰአት ኤዲሰን ካቫኒን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል። ተጨዋቹ በግል ከዩናይትድ ጋር ከስምምነት የደረሰ ሲሆን በቀጣዮቹ 48ሰአታት ውስጥ በማንችስተር ተገኝቶ ዝውውሩን እንደሚጨርስ ታውቋል። ተጨዋቹ በሪያል ማድሪድ እና በአትሌቲኮ ማድሪድ ሲፈለግ ቆይቶ ነበር።
የኢስፓኞሉ አማካይ ማርክ ሮካ ወደ ባየርን ሙኒክ የሚያደርገውን ዝውውር አጠናቋል። እንደ Sport ዘገባ ከሆነ ባየርኖች ለሮካ ዝውውር እስከ €15m ያወጡ ሲሆን ተጨዋቹ በሙኒክ ለቀጣይ አምስት አመታት ይቆያል።
የ31 አመቱ እንግሊዛዊው የኤቨርተን የመስመር አጥቂ ቲዮ ዋልኮት አሁን ላይ በበርካታ የእንግሊዝ ክለቦች እየተፈለገ ይገኛል። ተጨዋቹ ከኤቨርተን ለመልቀቅ ይፈልጋል።አሁን ላይ ዌስትሀም እና ክርስቲያል ፓላስ ተጨዋቹን ለማስፈረም ከኤቨርተን ጋር ንግግር ላይ ሲገኙ ፉልሀም እና ሳውዛንብተንንም የልጁ ፈላጊ ናቸው።
በርንሌዎች ወጣቱን የሊቨርፑል አማካይ ሀሪ ዊልሰንን ለማስፈረም ይፈልጋሉ። ሊቨርፑሎች ለተጨዋቹ የሚመጡ ጥያቄዎችን ለመስማት ዝግጁ ሲሆኑ ልጁ ላይ £15m ለጥፈውበታል።
ኤሲ ሚላኖች የዲያጎ ዳሎንትን ዝውውር ለመጨረስ ተቃርበዋል። ተጨዋቹ ዛሬ ከሰአት በሚላን ተገኝቶ የህክምና ምርመራውን በተሳካ ሁኔታ ያጠናቀቀ ሲሆን ነገ በይፋ የሚላን ተጨዋች ይሆናል። በተጨማሪም ሚላኖች የቸልሲውን ሩዲገር ለማስፈረም ለቸልሲ ጥያቄ ሊያቀርቡ ነው።
ናፖሊዎች የፈረንሳዊው የቸልሲ አማካይ ቲሞ ባካዮኮ ዝውውር ላይ እራሳቸውን አስገብተዋል። ተጨዋቹ አሁን ላይ በኤሲ ሚላን ቢፈለግም የኔፕልሱ ክለብ ባካዮኮን ለአንድ አመት በውሰት ለመውሰድ ይፈልጋሉ።
ፉልሀሞች የባርሴሎናውን ተከላካይ ቶዲቦን ዝውውር ወደ ማጠናቀቅ ተቃርበዋል።እንደ Sport ዘገባ ከሆነ ፉልሀሞች ለ20 አመቱ ተከላካይ £16m እንደሚከፍሉ ታውቋል።
No comments:
Post a Comment