ሌስተር ሲቲዎች ተከላካይ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።የሴንቲቲየኑ የ19 አመት ኮከብ ዌስሌይ ፎፋና በሌስተር ለአምስት አመታት ለመቆየት ፊርማውን አኑሯል።ልጁ በዚህ ክረምት በእንግሊዙ ዌስትሀም በጥብቅ ቢፈለግም አሁን ላይ ማረፊያው ኪንግ ፓዎር ሆኗል።
ማንችስተር ዩናይትዶች በመጨረሻ ሰአት ተጨዋቾችን ለማስፈረም እየሰሩ መሆኑ ተሰምቷል። ከሰሞኑ ስማቸው ከባርሳው ኦስማን ዴምቤሌ ጋር ሲያያዝ ቢቆይም አሁን ላይ ፊታቸውን ወደ ሲቪያው ሉካስ ኦካምፖስ ማዞራቸው ተሰምቷል።ሲቪያዎች ከልጅ 40ሚዩ ይፈልጋሉ ፥ ዩናይትዶች በተጨማሪም የአትላንታውን የ18 አመት ኮከብ አማድ ትራኦሬን ለማስፈረም ይፈልጋሉ።
ኢንተር ሚላኖች የቀድሞውን የማንችስተር ዩናይትድ የቀኝ መስመር ተከላካይ ዳርሚያንን ከፓርማ ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል። ተጨዋቹ ወደ ሚላን ዛሬ በመብረር የህክምና ምርመራውን በማድረግ ለኢንተር እስከ 2024 ፊርማውን እንደሚያኖር ታውቋል።ኢንተር ለተጨዋቹ ስንት እንደከፈለ ይፋ የሆነ ነገር የለም።
ቶተንሀሞች ሰኞ የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት የመሀል ተከላካይ ለማስፈረም እየሰሩ መሆኑ እርግጥ ሆኗል።ጆዜ ለረጅም ጊዜ ሲፈልገው የነበረውን የኢንተር ሚላኑን ሚላን ስክሪኒየርን ለማስፈረም ዛሬ ምሽት የተሻሻለ የዝውውር ገንዘብ ለኢንተር ለማቅረብ ይፈልጋሉ።
ያሳለፍነው አመት የፕሪሚየር ሊጉ ክስተት ክለብ የሆኑት ሼፊልድ ዩናይትዶች የአጥቂ መስመራቸውን ለማጠናከር ወጣቱን የሊቨርፑል አጥቂ ርሂአን ብሬውስተርን ለማስፈረም የመጨረሻ ምእራፍ ላይ ደርሰዋል። ለዝውውሩ ሼፊልዶች እስከ £23.5m እንደሚያወጡ ተረጋግጧል።
አርሰናሎች ፈረንሳዊውን የሊዮን አማካይ ኦሳም አዋርን ለማስፈረም የመጨረሻው ምእራፍ ላይ ደርሰዋል።እንደ እስፔኑ AS ዘገባ ከሆነ የሉካስ ቶሬራ ወደ አ.ማድሪድ መዘዋወር መቃረብ የአዋርን ዝውውር ያፋጥነዋል።ፒኤስጂ ባለቀ ሰአት ልጁን ለማስፈረም ጥረት ቢያደርግም ልጁ ከፈረንሳይ ሊግ መውጣትን ምርጫው አድርጓል።በዚህም ምክንያት መድፈኞቹ በመጨረሻ ሰአት አዋርን ሊያገኙ ተቃርበዋል።
ዌስትሀም ዩናይትዶች በመጨረሻም የስላቪያ ብራጉን ተከላካይ ቭላድሚር ኮፋልን ማስፈረማቸው ተረጋግጧል።መዶሻዎቹ ተጨዋቹን ለቀጣይ ሶስት አመታት በክለባቸው የሚያቆየውን ውል አስፈርመውታል።ዌስትሀሞች በቀጣይ የቸልሲውን አማካይ ሎፍተስቺክን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸው ታውቋል።
የጀርመኑ ሄርታ በርሊን የአለም ዋንጫ አሸናፊውን ማርዮ ጎትዜን በነፃ ለማስፈረም ተስፋን ሰንቀዋል። ተጨዋቹ ከዶርትመንድ ጋር ከተለያየ በሗላ እስካሁን ክለብ አልባ ሆኖ የቆየ ሲሆን አሁን ላይ ሄርታ በርሊኖች ልጁን ለማስፈረም ከፍተኛ እድል እንዳላቸው የጀርመኑ ቢልድ አስነብበዋል።
ሮማዎች ከማንችስተር ዩናይትድ ሁለት ተጨዋቾችን ለመውሰድ አሁንም ድርድር ላይ ናቸው። ቀዳሚው ክሪስ ስሞሊንግ ሲሆን የሱ ዝውውር እንደሚጠናቀቅ እርግጠኛ ናቸው።በተጨማሪም ግን የቀኝ መስመሩን ተከላካይ ዳሎትንም ሮማዎች ለመውሰድ ጥያቄ አቅርበው የዩናይትዶችን መልስ እየጠበቁ ነው።

it so nice
ReplyDelete