Thursday, October 1, 2020

የዕለተ ዓርብ ማለዳ ስፖርታዊ ዜናዎች

አቅራቢ - ኢብራሂም ሙሐመድ



 የአንቾሎቲው ኤቨርተን የተከላካይ ክፍላቸውን ለማጠናከር በክረምት የዝውውር መስኮት የተለያዩ ተጨዋቾችን ለማስፈረም ጥረት ሲያደርጉ ነበር።ሆኖም ኤቨርተኖች በስተመጨረሻ የኖርዊች ሲቲውን ተከላካይ ቤን ጎድፍሬን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል። ኤቨርተኖች ለተጨዋቹ እስከ £20m ሚከፍሉ ሲሆን ብቃቱ እየታየ የሚጨመር £6m ለመክፈል ተስማምተዋል። 





የሞይሱ ዌስትሀም ተጨማሪ የአማካይ ተጨዋቾችን ወደ ክለባቸው ማምጣት ይፈልጋሉ። አሁን ላይ በቸልሲ ብዙም የመሰለፍ እድል እያገኘ የማይገኘውን እንግሊዛዊውን ሎፍተስ ቺክን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል።ቸልሲዎች ተጨዋቹን በቋሚ ዝውውር ለመልቀቅ ፍላጎት የላቸውም። በተቃራኒው ዌስትሀሞች ልጁን ከውሰት ይልቅ በቋሚ ማስፈረም ነው ፍላጎታቸው። 




ቶተንሀሞች ብራዚላዊውን የቤኔፊካ አጥቂ ካርሎስ ቪኒሲየስን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል። እንደ ፖርቱጋላዊው ጋዜጠኛ Gonçalo Lopes ዘገባ ከሆነ ቶተንሀም እና ቤኔፊካ በ£45m ከስምምነት ደርሰዋል። ተጨዋቹ በሊቨርፑል እና በማንችስተር ዩናይትድ ቢፈለግም ማረፊያው ቶተንሀም ሊሆን ተቃርቧል። 





የስፔኑ ቫሌንሲያ ሳይጠበቅ የእንግሊዛዊው የቸልሲ አማካይ ድሪንክ ወተር ፈላጊ ሆነው ብቅ ብለዋል። ተጨዋቹ ያለፉትን አመታት በውሰት በአስቶንቪላ እና በበርንሌ ያልተሳካ ጊዜ ማሳለፉ ይታወቃል። አሁን ላይ ቫሌንሲያዎች ተጨዋቹን ከቸልሲ በውሰት ለማስፈረም ይፈልጋሉ። 





ባየርን ሙኒኮች የሎሬ ሳኔ ተደጋጋሚ ጉዳት በሱ ቦታ ሌላ ተጠባባቂ ተጨዋች ለማስፈረም ወደ ገበያው ወተዋል። ዛሬ ቢልድ እንዳስነበበው ባየርኖች የአትሌቲኮ ማድሪዱን ቶማስ ሌማርን በውሰት ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው። 





በአርቴታ ስር እንደማይፈለግ የተነገረው ፈረንሳዊው አማካይ ማቲዮ ጎንዶዚ ዝውውሩ ሳይጠናቀቅ ኢምሬትን ለመልቀቅ ዝግጁ ነው። ተጨዋቹ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ስሙ ሲነሳ ቆይቷል ዛሬ ላይ እንደተሰማው ግን የሀገሩ ክለብ የሆነው ማርሴይ ልጁን ለማስፈረም እንደሚፈልግ ታውቋል። 





የተከላይ ክፍላቸውን ለማጠናከር ተጨማሪ ተጨዋቾችን ለማስፈረም ወደ ገበያው የወጡት ማንችስተር ሲቲዎች የአያክሱን የግራ መስመር ተከላካይ ኒኮላስ ታግላፊኮን ለማስፈረም እስከ £22m ለመክፈል ዝግጁ ናቸው። ሲቲዎች ከታግላፊኮ በተጨማሪ የሙኒኩን ዳቪድ አላባንም ማስፈረም ይፈልጋሉ። 





የወልቨርሀምፕተኑ አምበል ኮኖር ኮአዲ በወልቭስ ለተጨማሪ አምስት አመታት ለመቆየት ፊርማውን አኑሯል።ከሊቨርፑል አካዳሚ የተገኘው የ27 አመቱ ተከላካይ ወልቭስን በ2015 ከሀደርስፊልድ የተቀላቀለ ሲሆን በሞሌክስ እስከ 2025 እንደሚቆይ ተረጋግጧል። 







ማንችስተር ዩናይትዶች በኦስማን ዴምቤሌ ዝውውር ጉዳይ ድርድር ላይ መሆናቸው ታውቋል። ዩናይትዶች ተጨዋቹን በውሰት ማስፈረም ሲፈልጉ በተቃራኒው ባርሳዎች ልጁን በቋሚ ዝውውር ነው መልቀቅ ሚፈልጉት። ዩናይትዶች እንደ አማራጭ የዋትፎርዱን እስማኤል ሳርን ይዘውታል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...