ሊቨርፑል እና ሪያል ማድሪድ በቀጣዩ የክረምት የዝውውር መስኮት ፈረንሳዊውን ወጣት ኮከብ ኪልያን ምባፔ ከፓሪሰን ዤርመን ለማዘዋወር እንደሚሰሩ ሌኪፕ አስነብቧል።
(L'Equipe - in French)
ሪያል ማድሪድ እንግሊዛዊውን አማካይ ዴሊ ዓሊ ከቶተንሃም የማዘዋወር ፍላጎት የለውም።
(Talksport)
ኤቨርተን ኮሎምቢያዊውን የመስመር ተከላካይ ሳንቲያጎ አሪያስ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ለማዘዋወር እየሰራ ነው።
(Liverpool Echo)
ማን ዩናይትድ ዶሚኒክ ካልቨርት ሊውንን ለማዘዋወር የሚፈልግ ከሆነ £80ሚ. ማቅረብ እንዳለበት ኤቨርተን ለቀያይ ሰይጣኖቹ አሳውቋል።
(Sun)
የፖርቶው የግራ መስመር ተከላካይ አሌክስ ቴላስ ወደ ማን ዩናይትድ ለመዘዋወር በግሉ የተስማማ ሲሆን ሁለቱ ክለቦች በዝውውሩ ሒሳብ ዙሪያ ድርድር ላይ ናቸው።
(Guardian)
ሲቪያ ጁሊየስ ካውንዴን እንደማይሸጥ ለማን ሲቲ አሳውቋል።የ21 አመቱ ፈረንሳዊ ኢንተርናሽናል በፔፕ ጋርዲዮላ በጥንቅ ነው የሚፈለገው።
(Goal)
ስፔናዊው አጥቂ አልቫሮ ሞራታ ወደ ቀድሞው ክለቡ ዩቬንትስ ሊመለስ ነው።ሞራታ በአትሌቲኮ ማድሪድ መልካም አመትን ነበር ያሳለፈው።
(Goal)
በሮናልድ ኪውመን ቦታ እንደሌለው የተነገረው ኡራጋዊው አጥቂ ሊውስ
ሱዋሬዝ ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ ሊዘዋወር ነው።
(RMC - via Mail)
አርሰናል ቶማስ ፓርቴይን ለማዘዋወር ከገንዘብ በተጨማሪ ሉካስ ቶሬራን ለአትሌቲኮ ማድሪስ ለመስጠት አቅዷል።
(El Gol - in Spanish
No comments:
Post a Comment