አዘጋጅ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
ማን ሲቲ ኻሊዱ ኩሊባሊን ለማዘዋወር ያደረገው ጥረት ባለመሳካቱ አይኑን ወደ ጁሊየስ ካውንዴ አዙሯል።በሲቪያ ድንቅ ጊዜን እያሳለፈ ያለው ካውንዴ ወደ ማን ሲቲ የሚዘዋወር ከሆነ የፔፕ ጋርዲዮላን የተከላካይ ክፍል እንደሚያጠናክረው ይጠበቃል።
(The Athletic)
ሊቨርፑል በዚህ የዝውውር መስኮት አሌክስ ኦክስሌድ ቼምበርሊንን የመሸጥ ፍላጎት የለውም።የቲዬጎ ሲልቫን ወደ አንፊልድ መምጣት ተከትሎ ቼምበርሊንን ዎልቭስ ሊያዘዋውረው ቢጥርም ሊቨርፑል ግን የመሸጥ ፍላጎት የለውም።
(The Mirror)
የጣሊያኖቹ ናፖሊ እና ላዚዮ ሺኾድራን ሙስጣፊን ከአርሰናል ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።አርሰናል ለተጨዋቹ ዝውውር £13ሚ. እንዲቀርብለት ይፈልጋል።
(The Sun)
ሮማ የሪያል ማድሪዱን አጥቂ ሉካ ዮቪች ለማዘዋወር እየሰራ ነው።ሮማ በቅድሚያ ግን አርካዲዬዝ ሜሊክን ከናፖሊ ለማዘዋወር ነው የሚሰራው።ማድሪድ ተጨዋቹን በውሰት ለመስጠት ይፈልጋል።
(Calcio Mercato)
ሊዮን የ23 አመቱ የኤሲ ሚላን ተጨዋች ሉካስ ፓኪዌይታ ለማዘዋወር እየሰራ ነው።ቫሌንሲያም በተጨማሪ የፓኪዌይታ ፈላጊ ነው።
(Calcio Mercator)
አርቶሮ ቪዳል ወደ ኢንተር ሚላን ሊዘዋወር መሆኑን ተከትሎ ሜሲ መልዕክቱን ልኮለታል።ሜሲ አብረው በባርሴሎና ለነበራቸው ጊዜ ቺሊያዊውን አማካይ አመስግኖታል።ቪዳል ዛሬ ኢንተር ሚላንን መቀላቀሉ ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል።
(Goal)
ዎልቭስ ፖርቱጋላዊውን የቀኝ መስመር ተከላካይ ኔልሰን ሴሜዶ ለማዘዋወር ከባርሴሎና ጋር ድርድር ጀምሯል።ዎልቭስ ወደ ስፐርስ የሸኘውን ማት ዶሀርቲን ቦታ ለመተካት ሴሜዶን በጥብቅ የሚፈልገው ሲሆን ለዝውውሩም £30ሚ. መድቧል።
(BBC Sport)
የዌስት ሀሙ አሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ ሶስት ወይም አራት ተጨማሪ ተጨዋቾችን ማዘዋወር እንደሚፈልግ ተናግሯል።የበርንሌው ተከላካይ ጄምስ ታርኮውስኪ ደግሞ አንዱ የሞይስ ምርጫ ነው።
(Standard)
"ማን ዩናይትድ ሳንቾ ሳይሆን የመሀል
ተከላካይ ነው ማስፈረም ያለበት" ጋሪ ኔቭል
የቀድሞው የማን ዩናይትድ ተጨዋች ጋሪ ኔቭል ትናንት በመክፈቻ ጨዋታ ማን ዩናይትድ በክሪስታል ፓላስ ከደረሰበት ሽንፈት በኋላ በሰጠው አስተያየት ፥ ቀያይ ሰይጣኖቹ ሳንቾን ከዶርትመንድ ለማዘዋወር ከመኳተን ይልቅ አንድ ሁነኛ የመሀል ተከላካይ ማስፈረም ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ አስተያየቱን ሰጥቷል።
ኔቭል ሀሪ ማጉዌይን እና ቪክተር ሊንደሎፍን ይዞ ፕሪሚየር ሊጉ ላይ ስኬታማ ለመሆን ማሰብ የዋህነት ነውም ብሏል።
በተለይ በትናንት ጨዋታ ደካማ የነበረውን ቪክቶር ሌንደሎፍን አብጠልጥሏል። "ለማን ዩናይትድ የሚመጥን ተጨዋች አይደለምም" ብሏል ኔቭል በአስተያየቱ።
ኔቭል በመጨረሻም ሊቨርፑል የሚፈልገውን ተጨዋች እያስፈረመ ነው ፥ ቼልሲ በወጣቶች ራሱን እየገነባ ነው ፥ ቶተንሃምም ጋሬዝ ቤልን አስፈርሟል ፥ ዩናይትድ ለምን በተሻለ መልኩ ራሱን አያጠናክርም? ሲል ጠይቋል።
No comments:
Post a Comment