የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከፍተኛ አምስት ተከፋይ ተጨዋቾች ዝርዝር
1.ፒዬር ኤምሪክ ኦባማያንግ (አርሰናል)
ከሳምንት በፊት አዲስ የሶስት አመት ኮንትራት የፈረመው ኦባማያንግ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከፍተኛ ተከፋይ ነው።ጋቦናዊው ኢንተርናሽናል ሳምታዊ £375,000 ነው የሚያገኘው።
2.ዴቪድ ዴሄያ (ማን ዩናይትድ)
ባለፈው አመት አዲስ ኮንትራት የፈረመው ስፔናዊው ግብ ጠባቂ ዴሄያ ከግብ ጠባቂዎች ከፍተኛው ተከፋይ ሲሆን ሳምንታዊ ደሞዙም ከኦባማያንግ እኩል £375,000 ነው።
3.ሜሱት ኦዚል (አርሰናል)
በመድፈኞቹ ያለው ቆይታ ጥያቄ ምልክት ውስጥ የገባው ጀርመናዊው አማካይ ሜሱት ኦዚል ሳምንታዊ £350,000 በማግኘት ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
4.ኬቨን ደ ብሮይነ (ማን ሲቲ)
ብዙዎችን በPerfection እያስደመመ ያለው ድንቁ ቤልጄሚያዊ አማካይ ኬቨን ደ ብሮይነ በሳምንት £330,000 ነው የሚያገኘው።
5.ካይ ሀቨርት (ቼልሲ)
ባሳለፍነው ሳምንት ቼልሲን የተቀላቀለው ጀርመናዊ የ21 አመት አማካይ ሳምንታዊ £310,000 በማግኘት አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
Note : ትናንት ቶተንሃምን የተቀላቀለው ጋሬዝ ቤል ስንት እንደሚከፈለው ይፋ አልሆነው።
No comments:
Post a Comment