Sunday, September 20, 2020

የዕለተ እሁድ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

 



ጋሬዝ ቤልን ያዘዋወረው ቶተንሃም እንግሊዛዊውን የማን ዩናይትድ የመስመር አጥቂ ጄሴ ሊንጋርድ ለማዘዋወር እየሰራ ነው።ለዝውውሩም £30ሚ. መድቧል።

(Daily Star Sunday)






ዌስት ሀም የ21 አመቱን እንግሊዛዊ አማካይ ዴክላን ሪስ እንደማይሸጠው ለቼልሲ አሳውቋል።

(90min)






ማን ሲቲ ፈረንሳዊውን የ21 አመት ተከላካይ ጁሌስ ካውንዴ ለማዘዋወር ያቀረበው €55ሚ. በሲቪያ ውድቅ ተደርጎበታል።ፔፕ ጋርዲዮላ ግን ተጨዋቹን በጥብቅ ይፈልገዋል።

(Marca)






ቼልሲ ሴኔጋላዊውን ግብ ጠባቂ ኤድዋርድ ሜንዲ ከኔንስ ለማዘዋወር ከስምምነት ላይ ደርሷል።የዝውውሩም ዋጋ £22ሚ. መሆኑ ተነግሯል።

(Observer)






ላሊጋ ውስጥ ባለው ጥብቅ የዝውውር ሕግ ምክንያት ባርሴሎና ኔዘርላንዳዊውን አማካይ ጆርጂንሆ ዋይናልደም ከሊቨርፑል ማዘዋወር አዳጋች ሆኖበታል።

(Sunday Mirror)






ዎልቭስ የ27 አመቱን እንግሊዛዊ አማካይ አሌክስ ኦክስሌድ ቼምበርሊን ከሊቨርፑል ለማዘዋወር ፍላጎት አለው።

(Sunday Mirror)






ሊድስ ዩናይትድ በማን ዩናይትድ የቋሚ ተሰላፊ ዕድል የተነፈገውን ዳኔል ጄምስ ለማዘዋወር እየሰራ ነው።ሶልሻየር ግን ዌልሳዊውን ኢንተርናሽናል ማቆየት ይፈልጋል።

(Daily Star Sunday)







ቫሌንሲያ አርጀንቲናዊውን ግብ ጠባቂ ሮሜሮ ለማዘዋወር ለማን ዩናይትድ €6ሚ. አቅርቧል።

(Sunday Mirror)







ስሙ ከኢንተር ሚላን እና ዩቬንትስ ጋር ሲያያዝ የነበረው ፈረንሳዊው አማካይ ታንጉይ ንዶምቤሌ በቶተንሃም እንደሚቆይ ተረጋግጧል።የዚህ ምክንያት ደግሞ ከጆዜ ሞሪንሆ ጋር በግል በስፋት ተነጋግሮ በመስማማቱ ነው።

(L'Equipe, via Football Italia)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...