Saturday, September 19, 2020

"ማን ዩናይትድ ሳንቾ ሳይሆን የመሀል ተከላካይ ነው ማስፈረም ያለበት" ጋሪ ኔቭል



"ማን ዩናይትድ ሳንቾ ሳይሆን የመሀል ተከላካይ ነው ማስፈረም ያለበት" ጋሪ ኔቭል



የቀድሞው የማን ዩናይትድ ተጨዋች ጋሪ ኔቭል ትናንት በመክፈቻ ጨዋታ ማን ዩናይትድ በክሪስታል ፓላስ ከደረሰበት ሽንፈት በኋላ በሰጠው አስተያየት ፥ ቀያይ ሰይጣኖቹ ሳንቾን ከዶርትመንድ ለማዘዋወር ከመኳተን ይልቅ አንድ ሁነኛ የመሀል ተከላካይ ማስፈረም ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ አስተያየቱን ሰጥቷል።



ኔቭል ሀሪ ማጉዌይን እና ቪክተር ሊንደሎፍን ይዞ ፕሪሚየር ሊጉ ላይ ስኬታማ ለመሆን ማሰብ የዋህነት ነውም ብሏል።


በተለይ በትናንት ጨዋታ ደካማ የነበረውን ቪክቶር ሌንደሎፍን አብጠልጥሏል። "ለማን ዩናይትድ የሚመጥን ተጨዋች አይደለምም" ብሏል ኔቭል በአስተያየቱ።



ኔቭል በመጨረሻም ሊቨርፑል የሚፈልገውን ተጨዋች  እያስፈረመ ነው ፥ ቼልሲ በወጣቶች ራሱን እየገነባ ነው ፥ ቶተንሃምም ጋሬዝ ቤልን አስፈርሟል ፥ ዩናይትድ ለምን በተሻለ መልኩ ራሱን አያጠናክርም? ሲል ጠይቋል።

 

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...