Saturday, October 10, 2020

የዕለተ እሁድ ማለዳ ስፖርታዊ ዜናዎች


በቀጣዩ የክረምት የዝውውር መስኮት ሊዮኔል ሜሲን ከባርሴሎና ለማዘዋወር ጠንክረው እንደሚሰሩ የማንቸስተር ሲቲው ቺፍ ኦፕሬቲንግ ኦፊሰር  ኦማር ቤራዳ ገልፀዋል። 

(Manchester Evening News) 

 

 

 

 

 

 

ኦሌ ጉናር ሶልሻየር አሁንም የእንግሊዛዊው የመስመር አጥቂ ጄደን ሳንቾ እና የኖርዌጅያኑ አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ ፈላጊ ነው ሲል ESPN አስነብቧል።ሁለቱም ተጨዋቾች በቦሩሲያ ዶርትመንድ እንደሚገኙ ይታወቃል። 

(ESPN) 

 

 

 

 

 

ፈረንሳዊው አማካይ ፖል ፖግባ በሪያል ማድሪድ መጫወት ሕልሙ መሆኑን መናገሩን ተከትሎ ሎስብላንኮዎቹ ዝውውሩን ከግብ ለማድረስ እየሰሩ ነው። 

(AS - in Spanish) 

 

 

 

 

 

ቤልጄሚያዊው አማካይ ኬቨን ደ ብሮይነ በማን ሲቲ ከተጨማሪ ሁለት አመታት የሚያቆየውን ኮንትራት ሊፈርም ነው።አዲሱ ውል ሳምንታዊ ደሞዙን ወደ £300,000 የሚያሳድግ ነው። 

(Sun)





ኡራጋዊው አጥቂ ሊውዝ ሱዋሬዝ ሊዮኔል ሜሲ ከባርሴሎና ለመውጣት ያለውን ፍላጎት በመደገፉ ለአትሌቲኮ ማድሪድ መሸ'ጡን ተናግሯል። 

(Express) 

 

 

 

ስፔናዊው አማካይ ሁዋን ማታ ከሳዑዲ አረቢያ ክለብ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ የሚያስገኝ ዝውውር ቢቀርብለትም በማን ዩናይትድ ለመቆየት ወስኗል። 

(Ian McGarry, via Mirror) 

 

 

 

 

 

 

ዌልሳዊው የመስመር አጥቂ ጋሬዝ ቤል የቶተንሃምን ማልያ ከዓመታት በኋላ ዳግም ለብሶ የመጀመሪያ ጨዋታውን በቀጣዩ ሳምንት ከዌስት ሀም ጋር ያደርጋል። 

(Telegraph) 

 

 

 

 

 

የማን ሲቲ የበላይ አመራሮች ፔፕ ጋርዲዮላ ከተጨማሪ አመታት በኤቲሀድ እንዲቆይ አዲስ ኮንትራት ሊያቀርቡለት ነው።ፔፕ ፍላጎት ከሌለው ግን አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም ዕቅድ አለው። 

(Telegraph)

 

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...