Tuesday, October 13, 2020

ከላምፓርድ ጋር መቃቃር ውስጥ የገባው ካንቴ ወደ ሪያል ማድሪድ?

አዘጋጅ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ከላምፓርድ ጋር መቃቃር ውስጥ የገባው ካንቴ ወደ ሪያል ማድሪድ?


ከላምፓርድ ወደ ስታንፎርድ ብሪጅ መምጣት በኋላ እምብዛም ደስተኛ ያልሆነው ፈረንሳዊው አማካይ ንጎሎ ካንቴ ትልቅ 'ሕልሙ' ወደ ነበረው ክለብ ፥ ወደ ሪያል ማድሪድ ሊያመራ እንደሚችል እየተዘገበ ነው።


Le Parisien እንደዘገበው ከቀናት በፊት ካንቴ በጓደኛው ሰርግ ላይ ለመገኘት ሲል ለላምፓርድ የአንድ ቀን ትሬኒንግ እንዲምረው ቢጠይቀውም ላምፓርድ ግን ውድቅ አድርጎበታል።


በዚህም ምክንያት ካንቴ ታላቅ ሕልሙ ወደ ነበረው ወደ በርናቢዮ ለመጓዝ ልብ መሸፈቱን ነው የፈረንሳዩ ሚዲያ Le Parisien አክሎ የዘገበው።


ካንቴ በስታንፎርድ ብሪጅ እስከ 2023 የሚያቆይ ኮንትራት ያለው ቢሆንም በቀጣዩ የዝውውር መስኮት ግን ቼልሲን መልቀቅ ይፈልጋል።

ካንቴ በሌስተር ስቲ ድንቅ አመትን ካሳለፈ በኋላ ወደ ቼልሲ መዘዋወሩ ይታወሳል።

 

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...