Tuesday, October 13, 2020

የዕለተ ማክሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

አዘጋጅ - ኢብራሒም ሙሐመድ


 

ማንችስተር ዩናይትዶች በቀጣይ የዝውውር መስኮቶች ከኩሊባሊ እና ከኡፓምካኖ አንዳቸውን ወደ ኦልትራፎርድ ማያዘዋውሩ ከሆነ በቀጣይ ጊዜያት የበርንሌውን ኮከብ ጀምስ ታርኮስኪን ለማስፈረም እንደሚፈልጉ ዘአትሌቲክ አስነብቧል። 






ፉልሀሞች የሀድርስፊልዱን ተከላካይ ቴሬንስ ኮንጎሎን ለማስፈረም ንግግር መጀመራቸውን ኤክስፕረስ ስፖርት አስነብቧል። ተጨዋቹ ከዚህ በፊት በፉልሀም ቤት በውሰት መቶ ነበር እናም ያን ተከትሎ ፉልሀሞች የእንግሊዝ የዝውውር መስኮት ሳይዘጋ ወደ ክራቨን ኮቴጅ ለመውሰድ እየሰሩ ይገኛሉ። ሀደርስፊልዶች ከልጁ ዝውውር £18m ይፈልጋሉ። 






ሁለቱ የቸልሲ ወጣት ኮከቦች ፊካዮ ቶሞሪ እና ቢሊ ጊሊሞር በጥር የዝውውር መስኮት ተጨማሪ የመጫወቻ ጊዜ ለማግኘት ቸልሲን እንደሚለቁ ለንደን ስታንዳርድ አስነብቧል። እንደ መረጃው ከሆነ ላምፓርድ ተጨዋቾቹ በጥር እንዲሄዱ ፈቅዷል።ኤቨርተን እና ዌስትሀም ልጆቹን ለማስፈረም ይፈልጋሉ። 






ሊቨርፑሎች የፕሪሚየር ሊግ ዝውውር ሳይጠናቀቅ ሁለተኛ ግብ ጠባቂያቸውን አድሪያንን ለመተካት ወደ ገበያ ወተዋል። በተለያየ ጊዜ ስህተቶችን እየሰራ የሚገኘውን  አድሪያንን ለመተካት ቀያዮቹ የዋትፎርዱን ግብ ጠባቂ ቤን ፎስተርን እና ጃክ ቡትላንድን የዝውውር ራዳራቸው ውስጥ አስገብተዋቸዋል። 






የኢንተር ሚላኑ አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ በቀጣይ ክረምት ፊት መስመራቸውን ለማጠናከር አርጀንቲናዊውን የማንችስተር ሲቲ አጥቂ ኩን አግዌሮን ከኢትሀድ ለመውሰድ ፍላጎት አላቸው። እንደ CalcioMercato ዘገባ ከሆነ ኢንተሮች አጉዌሮን ማስፈረም ከቻሉ ማርቲኔዝን ለመልቀቅ ዝግጁ ናቸው። 






ማንችስተር ሲቲዎች የግራ መስመር ተከላካይ ለማስፈረም ወደ ገበያ በጥር ሊወጡ እንደተዘጋጁ The Sun አስነብቧል።በሜንዲ እና በዚንቼንኮ እምነት ያጣው ጋርዲዮላ ተጨማሪ የግራ መስመር ተከላካይ ለማስፈረም ይፈልጋል። እንደ መረጃው ከሆነ ፔፕ የአያክሱን  ፉልባክ ኒኮላስ ታግላፊኮን ማስፈረም ነው ሚፈልገው። ሲቲ ለልጁ £23m ለመክፈል ዝግጁ ናቸው። 





በመጨረሻም ዊሊያም ሳሊባ በአርሰናል እንደሚቆይ ዘአትሌቲክ አስነብቧል። ከሴንቲቲየን ከመጣ በሗላ በአርቴታ ስር እምነት ያላገኘው ወጣቱ ተከላካይ በውሰት ለሻንፒዮን ሺፕ ክለቦች ሊሰጥ እንደሚችል ቢወራም በመጨረሻም አርሰናሎች ለተጨዋቹ እስከ ግማሽ ሲዝን እድል በመስጠት ሊያዩት እንደፈለጉ ታውቋል።ነገር ግን በልጁ ደስተኛ ካልሆኑ በጥር በውሰት እንደሚሰጥ እርግጥ ሆኗል። 






ዌስትሀም ዩናይትዶች ተጨማሪ ተከላካይ ለማስፈረም ወደ ገበያው ወተዋል።መዶሻዎቹ የዌስትብሮሙን ተከላካይ ክራግ ዳውሰንን ለማስፈረም ንግግር ላይ መሆናቸውን ስካይ ስፖርት ይፋ አድርጓል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...