አዘጋጅ - ኢብራሒም ሙሐመድ
ማንችስተር ሲቲዎች ይሄ የውድድር አመት ሲጠናቀቅ ፔፕ ጋርዲዮላን በማሰናበት አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ይፈልጋሉ። እንደ ዴይሊ ሜይል ዘገባ ከሆነ ሲቲዎች የመጀመሪያ የአሰልጣኝ ምርጫቸው ማውሪሲዮ ፖቸቲንሆን ያረጉ ሲሆን በተጨማሪም ወጣቱን የሌብዢክ አሰልጣኝ ጁሊያን ሌንግልስማንን እንደ አማራጭ ይዘውታል።
ይሄን አመት በሊዮን ማሳለፍ እንደሚፈልግ ተናግሮ ዝውውሮችን ውድቅ ያደረገው ፈረንሳዊው አማካይ ሆሳም አዋር በጥር የዝውውር መስኮት ወደ ሌላ ክለብ የማቅናት እድል እንዳለው ሌኪፕ አስነብቧል። ተጨዋቹ በአርሰናል በጥብቅ ቢፈለግም የልጁ ፍላጎት በቻምፒየንስ ሊግ ክለብ መጫወት ሆኗል። ይህን ተከትሎ ከአርሰናል በተጨማሪ ለሚፈልጉት ፒኤስጂ እና ጁቬንቱስ ማንቂያ ደውል ሆኖላቸዋል።
አስቀያሚ የውድድር አመትን እያሳለፉ የሚገኙት ሼፊልድ ዩናይትዶች በቅርብ ቀናት ከዩናይትድ ከቻምፒየንስ ሊግ እና ከፕሪሚየር ሊግ ስብስብ ውጭ የሆነውን ማርኮስ ሮኾን በጥር በውሰት ለመውሰድ ፍላጎት አሳይተዋል። ዩናይትዶች በተቃራኒው ልጁን በቋሚ ዝውውር ነው ለመልቀቅ የፈለጉት።
ተከላካያቸውን ቨርጅል ቫንዳይክን በዚህ አመት በድጋሚ በሜዳ እንደማያዩት ያረጋገጡት ሊቨርፑሎች በጥር የዝውውር መስኮት ሌላ ተከላካይ ለማስፈረም ይፈልጋሉ። እንደ ሚረር ዘገባ ከሆነ ሊቨርፑሎች £20m በመክፈል ቱርካዊውን የሻልክ04 ተከላካይ ኦዛን ካባክን ለማምጣት ይፈልጋሉ።ነገር ግን ሻልኮች ተጨዋቹን ከ£30m በታች እንደማይሸጡት ይፋ አርገዋል።
ባርሴሎና እና ጁቬንቱስ ወጣቱን የአያክስ አማካይ ርያን ግራቨንበርችን ለማስፈረም አይናቸውን ጥለዋል። ወጣቱ የ18 አመት አማካይ በዘንድሮ ሲዝን በአያክስ እየታዩ ካሉ ተጨዋቾች ቀዳሚው ሆኗል። ተጨዋቹ በዚህ ሲዝን ለአያክስ ሁለት ለግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።
ዌስትሀሞች የ21 አመቱን እንግሊዛዊ አማካያቸውን ዴክላን ራይስ ኮንትራት ለማደስ ፍላጎት አላቸው። ተጨዋቹ በቸልሲ እጅጉኑ መፈለጉን ተከትሎ ዌስትሀሞች ለተጨዋቹ ሳምንታዊ £60,000ፓ በመክፈል ኮንትራቱን እስከ 2025 ለማራዘም ለተጨዋቹ ይፋዊ ጥያቄ አቅርበውለታል።
አርሰናሎች የቀድሞ ልጃቸውን አሁን በሆላንዱ ፒኤስቪ አይንድሆቨን ድንቅ ጊዜ እያሳለፈ ሚገኘውን ዶንየል ማለንን በድጋሚ ወደ ኢምሬት ለመመለስ ፍላጎት አሳይተዋል።አርሰናሎች ተጨዋቹን ከሶስት አመት በፊት በ£540,000ፓ የሸጡት ሲሆን ማለን በፒኤስቪ በ78ጨዋታ 49ጎሎችን አስቆጥሯል። ልጁ በጁቬንቱስ እና በባርሴሎናም ይፈለጋል።
የማንችስተር ዩናይትዱ ግብ ጠባቂ ሰርጂዮ ሮሞሮ በዩናይትድ ቦርድ እጅጉኑ ተበሳጭቷል። የሄንደርሰን ከሼፊልድ መምጣትን ተከትሎ በዩናይትድ እንደማይፈለግ የተነገረው ሮሜሮ ዩናይትዶች ኮንትራቱን እንዲያቋርጡለት እና ወደፈለገበት ክለብ መሄድ እንዲችል በጥቂት ቀናት ውስጥ ይፋዊ ጥያቄ ለማቅረብ መዘጋጀቱን M.E.N አስነብቧል።
No comments:
Post a Comment