Wednesday, October 28, 2020

የዕለተ ረቡዕ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

አዘጋጅ - ኢብራሂም ሙሐመድ


 

የዶርትመንዱ አጥቂ ሀላንድ አሁንም የሶልሻየር ቁጥር አንድ ምርጫ ነው። በግልም ሁለቱም ግንኙነት አላቸው። ያለፈው ዝውውርም ያልተሳካው በወኪሉ ሚኖ ራዮላ ጋር ባለ ምክንያት እንደሆነ ተዘግቧል።






ፈረንሳዊው የሪያል ማድሪድ አጥቂ ካሪም ቤንዜማ በሪያል ማድሪድ ቆይታው እርግጠኛ አልሆነም። እንደ AS ዘገባ ከሆነ ቤንዜማ የሀገሩ ልጅ ምባፔ በክረምት ቤርናቦ ሚደርስ ከሆነ ቤንዜማ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ለማምራት ይፈልጋል። 






ኤቨርተኖች ኮሎምቢያዊውን የቶተንሀም የመሀል ተከላካይ ዳቪንሰን ሳንቼዝን ለማስፈረም ይፈልጋሉ። አንቾሎቲም ተጨዋቹን ለመውሰድ የሀገሩን ልጅ ሀሜስ ሮድሪጌዝን እንዲያግባባው እንደሚጠቀሙበት ይጠበቃል። 






ኤሲ ሚላኖች አሁንም ተጨማሪ አጥቂ ለማስፈረም ይፈልጋሉ። ሚላኖች በቀጣዩ ክረምት ዋነኛ ኢላማቸው የቀድሞ የከተማ ተቀናቃኛቸው የኢንተር ሚላኑ አጥቂ ማውሮ ኢካርዲ ሆኗል። በፒኤስጂ እንደተጠበቀው ያልሆነው ኢካርዲ በድጋሚ ወደ ጣሊያንን ሊመለስ እንደሚችል ይጠበቃል። 






የጆዜው ቶተንሀም በጥር ተጨማሪ አማካዮችን ወደ ስፐርስ ለማምጣት ይፈልጋሉ። የሞሪንሆም የመጀመሪያ ምርጫ የ22 አመቱ የባርሴሎና አማካይ ካርለስ አሌና ሆኗል። ባሳለፍነው ሲዝን ግማሽ አመት ላይ ለሪያል ቤትስ በውሰት መሰጠቱ ይታወሳል። 






ጁቬንቱሶች የላላውን የተከላካይ መስመራቸውን ለማጠናከር ጣሊያን ከሚገኙ ክለቦች ተጨዋች ለማስፈረም ይፈልጋሉ። እንደ Calcio Mercato ዘገባ ከሆነ ጁቬዎች የቬሮናውን የ20 አመቱን ማቲዮ ሎቫቶን ዋነኛ ኢላማቸው ያደረጉት ተጨዋቹም ባሳለፍነው እሁድ ጁቬንቱስን ከገጠመው ቡድን ውስጥ ነበር። 






ባሳለፍነው ሲዝን በጥር የዝውውር መስኮት ቶተንሀምን ለቆ ኢንተር ሚላንን የተቀላቀለው ክርስቲያን ኤሪክሰን በጣሊያን ምቾት እየተሰማው አይደለም። ይህንን ተከትሎ ኤሪክሰን በጥር ኢንተርን ለቆ መውጣት ይፈልጋል። እስካሁን ኤሪክሰንን ብሎ የመጣ ክለብ ባይኖርም የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ የልጁ ማረፊያ ሊሆን ይችላል። 







አርሰናሎች ለጀርመናዊው ተከላካይ ሽኩድራን ሙስጣፊ ያቀረቡት አዲስ ኮንትራት ማራዘሚያ ጥያቄ በሙስጣፊ ውድቅ ተደርጎባቸውል። ሙስጣፊ በክረምት አርሰናልን መልቀቅ ይፈልጋል። ሙስጣፊ አርሰናልን በ2016 ከቫሌንሲያ ተቀላቅሎ ለአርሰናል 143 ጨዋታዎችን አድርጓል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...