አዘጋጅ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
ዛሬ ከባርሴሎና ጋር በሚደረገው ጨዋታ ሮናልዶ ይሰለፋል?
ዛሬ ምሽት በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ ዩቬንትስ በሜዳው ባርሴሎናን የሚያስተናግድ ሲሆን የፖርቱጋላዊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በጨዋታው መሰለፍ አለመሰለፍም ይፋ ሆኗል።
ዩቬ ይፋ ባደረገው መሰረት ሮናልዶ በኮቪድ 19 ምክንያት የዛሬው ጨዋታ የሚያልፈው ይሆናል።በዚህም ሮናልዶ እና ሜሲ ከብዙ ጊዜ በኃላ በአንድ ሜዳ ማየት ለሻቱ ሰዎች አሳዛኝ ሆኗል።
ሮናልዶ መጀመሪያ ፖርቱጋል ከ ፈረንሳይ ካደረገችው ጨዋታ በኋላ ኮቪድ 19 የተገኘበት ሲሆን እስከ አሁን ሶስት ጨዋታዎች አምልጠውታል ፥ አንድ የፖርቱጋል ሁለት የዩቬንትስ።
No comments:
Post a Comment