ማን ዩናይትድ ብራዚላዊውን ተከላካይ አሌክስ ቴሌስ ከፖርቶ በማዘዋወር የአምስት አመት ኮንትራት ሊያስፈርመው መስማማቱን ስፖርት አስነብቧል።የ27 አመቱ ተከላካይ በፓሪሰን ዤርመንም በጥብቅ ይፈለጋል።
(RMC Sport)
ቶተንሃም ዌልሳዊውን የመስመር አጥቂ ጋሬዝ ቤል ለአንድ አመት በውሰት ለመውሰድ ጥያቄ አቅርቧል።ስፐርስ ለሁለት መንፈቅ ውሰቱ ለሎስብላንኮዎቹ £9ሚ. አሰናድታለች።
(The Telegraph)
ኢንተር ሚላን የማን ዩናይትዱን እንግሊዛዊ ተከላካይ ክሪስ ስሞሊንግ ለአንድ አመት በውሰት ለመውሰድ ጥያቄ አቅርቧል።ስሞሊንግ ያለፈውን አመት በሮማ ማሳለፉ ይታወሳል።
(The Sun)
በባርሴሎና እና በባየርን ሙኒክ በጥብቅ እየተፈለገ ያለው የመስመር ተከላካዩ ሰርጂዮ ደስት በአያክስ እንደሚቆይ አሰልጣኙ ኤሪክ ቴን ሀግ አሳውቋል።
(Goal)
ቲዬጎ አልካንታራን ያዘዋወረው ሊቨርፑል የአጥቂ መስመሩን ይበልጥ ለማጠናከር ዲዬጎ ጆታን ከዎልቭስ ለማዘዋወር እየሰራ ነው።ክሎፕ ጆታን የሳላህ እና ማኔ ተጠባባቂ ለማድረግ ነው ያቀዱት።
(Goal)
ሊቨርፑል ፈረንሳዊውን የመስመር አጥቂ ኦስማን ዴምቤሌ በውሰት ለመውሰድ ባርሴሎናን ጠይቋል።ሮናልድ ኪውመን በተጨዋቹ ዙሪያ ያላቸው አቋም ግልፅ አይደለም።
(Sport)
ማን ሲቲ ፈረንሳዊውን ተከላካይ ጁሊየስ ላውንዴ ከሲቪያ ለማዘዋወር እየሰራ ነው።አርጀንቲናዊውን ኒኮላስ ኦታሜንዲንም የዝውውሩ አካል አድርጎ ወደ ስፔን መሸኘት ይፈልጋል።
(Telegraph)
የማርሴሎ ቢዬልሳው ክለብ ሊድስ ዩናይትድ የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት አርጀንቲናዊውን አማካይ ሮድሪጎ ደ ፓውል ከዩዲኒዜ ለማዘዋወር እየሰራ ነው።
(Fabrizio Romano)
No comments:
Post a Comment