አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
ማን ዩናይትድ እንግሊዛዊውን የመስመር አጥቂ ጄደን ሳንቾ ለማዘዋወር የሚያደርገው ጥረት ካልሰመረለት የዋትፎርዱን ኤስማሊያ ሳር እንደ አማራጭ ይመለከታል።ሳር በሊቨርፑልም ጭምር ይፈለጋል።
(Independent)
ሴኔጋላዊው ግብ ጠባቂ ኤድዋርድ ሜንድ ከሬንስ ለቆ ቼልሲን ለመቀላቀል ከስምምነት ላይ መድረሱን የተጨዋቹ ወኪል ይፋ አድርጓል።
(Stades via Star)
በርካታ ዝውውሮችን በጊዜ እየጨረሰ ያለው ቼልሲ የዌስት ሀሙን እንግሊዛዊ አማካይ ዴክላን ራይስ ለማዘዋወር እየሰራ ነው።ለሰማያዊዎቹ ይህ ዝውውሩ የመጨረሻ እንደሚሆን ይጠበቃል።
(Simon Phillips via Express)
ሌስተር ሲቲ ቱርካዊውን አጥቂ ሼንጊዝ አንደር ከሮማ በውሰት ለማዘዋወር ከስምምነት ላይ ደርሷል።ብሬንደን ሮጀርስ የበርንሌይውን ተከላካይ ጄምስ ታራኮውስኪም ይፈልጋሉ።
(Sky Sports)
አርሰናል ፈረንሳዊውን የሊዮን አማካይ ሆሰም አውራ ለማዘዋወር ከተጨዋቹ ጋር በግል ተነጋግሮ ከስምምነት ላይ መድረሱን ስታር አስነብቧል።
(Star)
እንግሊዛዊው የቶተንሃም አማካይ ዴሊ ዓሊ በፈረንሳዩ ክለብ ፓሪሰን ዤርመን እና በጣሊያኑ ክለብ ኢንተር ሚላን እየተፈለገ ይገኛል።
(Mail)
ቦሲኒያዊው አጥቂ ኤዲን ዜኮ ዩቬንትስን በሁለት አመት ውል እንደሚቀላቀል የጣሊያን ሚዲያዎች እየዘገቡ ነው።ይህም የሊውስ ሱዋሬዝን ወደ ዪቬንትስ መቀላቀል ያበቃ ነው አስብሎታል።
(Goal)
ማን ዩናይትድ የሶስት ተጨዋቾችን ዝውውር ለመጨረስ እየሰራ ነው።ሶስቱ ዝውውሮች ኢቫን ፔሪሲች ከኢንተር ሚላን ፣ ኪንግስሊ ኮማን ከባየርን ሙኒክ እና ዳግላስ ኮስታ በዩቬንትስ ናቸው።
(ESPN)
No comments:
Post a Comment