Wednesday, September 16, 2020

የዕለተ ረቡዕ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች



ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ በአርሰናል ለተጨማሪ ሶስት አመታት የሚያቆየውን ኮንትራት ፈርሟል።በስምምነቱ መሰረት ጋቦናዊው አጥቂ ቦነስን ጨምሮ በነዚህ አመታት £55ሚ.  የሚያገኝ ይሆናል።
(Times - subscription required)





አርሰናል የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት ቶማስ ፓርቲን ከአትሌቲኮ ማድሪድ ሆሰም ኦሪየን ከሊዮን ለማዘዋወር እየሰራ ነው።
(Mirror)





ባየርን ሙኒክ ከቼልሲ አካዳሚ ያደገውን ካሉም ሂውድሰን ኦዶይን ለማዘዋወር እየሰራ ነው።ፍራንክ ላምፓርድ ግን የ19 አመቱን እንግሊዛዊ የመሸጥ ፍላጎት የለውም።
(Mail)





ቶተንሃም ጣሊያናዊውን አጥቂ አንድሪያ ቤሎቲ ከቶሪኖ በውሰት ለመውሰድ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ ሆኗል።ቶሪኖ በግዢ ከሆነ ፍቃደኛ የሆነ ሲሆን £50ሚ. ለዝውውሩ ይፈልጋል።
(Express)





ባርሴሎና ኔዘርላንዳዊውን የመስመር አጥቂ ሜንፊስ ዴፓይ ከሊዮን ለማዘዋወር ፍላጎት ያለው ሲሆን ከዛ በፊት ግን አንዳንድ ተጨዋቾችን ለመሸጥ ይፈልጋል።
(Fox Sports Netherlands)





ዪቬንትስ ኡራጋዊውን አጥቂ ሊውዝ ሱዋሬዝ ከባርሴሎና ለማዘዋወር እያደረገ ያለው ጥረት መጓተቱን ተከትሎ ሌላ አማራጭ ለመመልከት እየሞከረ ነው።
(Goal)





ኢንተት ሚላን የመስመር ተከላካዩን ኤመርሰን ፓልሜሪ ለማዘዋወር ጥረት እያደረገ ቢሆንም ተጨዋቹ በውሰት ዌስት ሀምን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል።
(Independent)





ቶተንሃም ሆትስፐር የቀድሞው ተጨዋቹን  ጋሬዝ ቤልን ከሪያል ማድሪድ ለማዘዋወር ከገንዘብ በተጨማሪ ዴሊ አሊን የዝውውሩ አካል ለማድረግ እየሰራ ነው።
(Mail)





ኤቨርተን በርከት ያሉ ተጨዋቾችን ለመሸጥ ወስኖ ጥያቄዎችን ለመቀበል ተዘጋጅቷል።ከሚሸጡት ተጨዋቾች መሀከል ቲዮ ዋልኮት ፣ አሌክስ ኢዮቢ እና ሞይስ ኪን ተካተውበታል።
(Mirror)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...