አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ
ኤቨርተኖች ብራዚላዊውን የናፖሊ አማካይ ጆይ አለንን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።ናፖሊዎች ከተጨዋቹ እስከ €25m +€3m ይፈልጋሉ።ኤቨርተኖችም ለመክፈል ፍቃደኛ ሆነዋል ተጨዋቹም በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ እንግሊዝ በመምጣት ምርመራውን ያደርጋል።
ማንችስተር ዩናይትድ እና አያክስ አምስተርዳም በሆላንዳዊው አማካይ ጆኒ ቫንድቢክ ዝውውር ላይ ከስምምነት ደርሰዋል።ዩናይትዶች ለልጁ እስከ £40m ይከፍላሉ። ቫንድቢክ በ72 ሰአታት ውስጥ ወደ ማንችስተር ከተማ በመብረር ዝውውሩን እንደሚጨርስ ታውቋል።
ኢንተር ሚላኖች የጣሊያናዊውን የ20 አመት የብሬሺያ አማካይ ሳንድሮ ቶናሊን ዝውውር መጨረሳቸው ታውቋል።ሚላኖች ለወጣቱ አማካይ ለብሬሺያ እስከ £30m እንደከፈሉ ሲታወቅ በሚላን የአምስት አመት ኮንትራት ተሰቶታል።ነገር ግን ይህን አመት በብሬሺያ በውሰት እንደሚያሳልፍ ይፋ ተደርጓል።
ኒውካስትሎች ከቀናት በፊት ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ሄዶ መጫወት እንደሚፈልግ የተናገረውን የፖርቶ አጥቂ ሙሳ ማሬጋን ለማስፈረም ፈላጊ ክለብ ሆነው መተዋል። ኒውካስትሎች ከሁሉም ክለቦች የተሻለ ልጁን የማስፈረም እድል አግኝተዋል።ፖርቶዎች ከተጨዋቹ £20m ይፈልጋሉ ዌስትሀሞችም የልጁ ፈላጊ ናቸው።
አስቶንቪላዎች አዲስ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ወደ ገበያው ወተዋል። ስማቸው ከተለያዩ ግብ ጠባቂዎች ጋር ቢነሳም አሁን ላይ ሙሉ ትኩረታቸውን አርጀንቲናዊው የአርሰናል ሁለተኛ ግብ ጠባቂ ማርቲኔዝ ላይ አርገዋል። ቪላዎች ለ27 አመቱ ኮከብ እስከ £10m መክፈል ይፈልጋሉ።
ግብ ጠባቂያቸውን ኤዱአርድ ሜንዲን በቸልሲ ሊነጠቁ የተቃረቡት ሬንሶች በሱ ምትክ የዘንድሮውን ሲዝን በሪያል ማድሪድ የኩርቱዋ ተጠባባቂ ሆኖ ያሳለፈውን የፒኤስጂውን ግብ ጠባቂ አልፖንሴ አሪዮላን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል።በተጨማሪም በጥቂት ቀናት አሪዮላ ቸልሲን ይቀላቀላል።
በቀጣይ አመት ከወልቭስ ጋር ኮንትራታቸው የሚጠናቀቀው ኑኖ እስፕሪትቶ ሳንቼዝ ተጨማሪ ኮንትራት ከወልቭስ እንደቀረበላቸው ሚረር አስነብቧል።ወልቭሶች ለአሰልጣኙ የሶስት አመት ኮንትራት ሰተውታል።
ጋላታሳራዮች የማንችስተር ዩናይትዱን የ27 አመት ብራዚላዊውን አማካይ ፍሬድን በውሰት ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው። በቀናት ውስጥ ለማንችስተር ይፋዊ ጥያቄ ለማቅረብ ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል።
No comments:
Post a Comment