Friday, August 28, 2020

የዕለተ አርብ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

                 አዘጋጅ - ኢብራሒም ሙሐመድ


ማንችስተር ዩናይትዶች የተከላካይ ክፍላቸውን ለማጠናከር አሁንም የተለያዩ ተጨዋቾችን እየተመለከቱ ይገኛሉ። እንደ M.E.N ዘገባ ከሆነ ዩናይትዶች የሞናኮውን ወጣት ተከላካይ ቤኖይት ባዲያሺሌ ለማስፈረም ጥያቄ አቅርበው ውድቅ ተደርጎባቸዋል።ዩናይትድ ለልጅ £22m ያቀረቡ ሲሆን ሞናኮዎች ከተጨዋቹ እስከ £35m ይፈልጋሉ።





ባርሴሎናዎች ሊዮኔል ሜሲን ሚለቁ ከሆነ በሱ ምትክ ሴኔጋላዊውን የሊቨርፑል ኮከብ ሳይዶ ማኔን ለማስፈረም ይፈልጋሉ።ኩዩማን ከዚህ በፊት ከልጁ ጋር የሰሩ ሲሆን በድጋሚ ከማኔ ጋር ለመገናኘት ይፈልጋሉ።ለተጨዋቹ ባርሴሎናዎች እስከ £100m ይፈልጋሉ።





ማንችስተር ሲቲዎች ሊዮኔል ሜሲን ለማስፈረም በይፋ ጥያቄ ሊያቀርቡ ነው።እንደ ዴይሊ ሜል ዘገባ ከሆነ ማንችስተር ሲቲዎች ለባርሴሎናዎች ጋብርኤል ጄሱስ እና በርናንዶ ሲልቫ በተጨማሪም ገንዘብ በመስጠት ሊዮኔል ሜሲን ለማስፈረም ጥያቄ ሊያቀርቡ ነው።





ቼልሲዎች የብራዚላዊውን ተከላካይ ቲያጎ ሲልቫን ዝውውር መጨረሳቸውን ይፋ አድርገዋል። ተጨዋቹ ዛሬ ከሰአት የቸልሲ ንብረት መሆኑ ሲረጋገጥ ቸልሲዎች በተጨማሪ የካይ ሀቨርትዝን ዝውውር ለመጨረስ የመጨረሻ ድርድር ላይ መሆናቸው ታውቋል።






ያለፉትን አስር አመታት በቪካሬጅ ሮድ ያሳለፈው የዋትፎርዱ አጥቂ ትሮይ ዲኔ በመጨረሻም ከዋትፎርድ ጋር ሊለያይ ተቃርቧል። አዲስ ሊቀላቀል የሚፈልግበት ክለብ ዘንድሮ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ያደገው ዌስትብሮሚች አልቢዮን ሆኗል። የ32 አመቱ አጥቂ በጥቂት ቀናት የመጨረሻ ማረፊያው ይታወቃል።





ቤን ቺልዌልን ለቸልሲ አሳልፈው የሰጡት ሌስተር ሲቲዎች በሱ ቦታ ሌላ የግራ መስመር ተከላካይ ለማስፈረም ወደ ገበያ ወተዋል። ሌስተሮች አይናቸውን የአያክሱ የመስመር ተከላካይ ኒኮላስ ታግላፊኮ አልያም የአትላንታ ሮቢን ጎሰልስን ለማስፈረም  እንቅስቃሴ ጀምረዋል።





ቸልሲዎች እንግሊዛዊውን አማካይ ዴክላን ራይስን ከዌስትሀም ለማስፈረም ዝግጁ ሆነዋል።እንደ Football Insider claims ዘገባ ከሆነ ቸልሲዎች በ2017 ከሌስተር ያስፈረሙትን ኒጎሎ ካንቴን በመቀልቅ በምትኩ ራይስን ለማስፈረም ይፈልጋሉ።





ኢንተር ሚላኖች በተለያዩ ክለቦች ሲፈለግ የነበረውን ጣሊያኖች አዲሱ ፒርሎ ሚሉትን የብሬሲያውን አማካይ ሳንድሮ ቶናሊን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል።እንደ Corriere dello Sport ዘገባ ዩናይትዶች ዝውውሩ ላይ ቢገቡበትም ኢንተርሚላኖች ለብሬሺያ €40m በመክፈል ተጨዋቹን ሊወስዱት ተቃርበዋል።





የፖርቱጋሉ ክለብ ቤኔፊካ የሪያል ማድሪዱን የመስመር አጥቂ ማርያኖ ዲያዝ ያቀረበው የውሰት ጥያቄ በማድሪድ ተቀባይነት አግኝቷል።እንደ Record ዘገባ ከሆነ ማድሪድ እና ቤኔፊካ በልጁ ዝውውር ጉዳይ ላይ ከስምምነት ደርሰዋል። የውሰት ዝውውሩ በዚህ ሳምንት ይጠናቀቃል።





ሙሳ ማሬጋ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች መዘዋወር እንደሚፈልግ ተናግሯል።የ29 አመቱ ኮከብ በፖርቶ የቀረው የአንድ አመት ኮንትራት ብቻ ነው።እንደ A Bola ዘገባ ከሆነ ተጨዋቹ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ስሙ ሲያያዝ ቆይቷል ልጁ በማንችስተር እና ቸልሲም ይፈለጋል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...