Thursday, August 27, 2020

የዕለተ ሐሙስ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

             አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)




ሊዮኔል ሜሲ ከባርሴሎና ጋር እንደሚለያይ መረጋገጡን ተከትሎ ቀጣይ ማረፊያው የት ይሆናል የሚለው ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኗል።ሰን ዛሬ እንዳስነበበው ከሆነ የ33 አመቱ አርጀንቲናዊ አባት ከማን ሲቲ ጋር ከመደራደር እንግሊዝ ነው የሚገኘው።የካታላኑ ጋዜጣ ስፖርት ደግሞ ሜሲ በቀጣዩ ሰኞ ከባርሴሎና ጋር የነበረውን ሕጋዊ ጉዳይ ለመጨረስ ይገናኛል ብሏል።ሜሲ ማን ሲቲን የሚቀላቀል ከሆነ አመታዊ £90ሚ. በደሞዝ መልክ ብቻ እንደሚያገኝ ተዘግቧል።
(SUN)





ኤክስፕረስ በማለዳ ዘገባው እንደገለጸው ማን ዩናይትድ አሁንም ጄደን ሳንቾን ከቦሩሲያ ዶርትመንድ ለማዘዋወር በመስራት ላይ ይገኛል።ቀያይ ሰይጣኖቹ የሜሲንም ጉዳይ በአጽንኦት በመመልከት ላይ ናቸው።
(Express)





አዲሱ የባርሴሎና አሰልጣኝ ሮናልድ ኪውመን ባሳለፍነው ሰኞ በግል  ኡራጋዊውን አጥቂ ሊውስ ሱዋሬዝ ጠርቶ ከዚህ በኋላ በክለቡ ቦታ እንደሌለው እና ክለብ እንዲፈልግ ነግሮታል።
(Mail)





ብራዚላዊው ተከላካይ ቲዬጎ ሲልቫ ቼልሲን ለመቀላቀል በዛሬው ዕለት የህክምና ምርመራ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።የ35 አመቱ ተከላካይ በፓሪሰን ዤርመን አዲስ ውል ቀርቦለት የነበረ ቢሆንም ውድቅ አድርጎታል።
(Sky Sports)






ቼልሲ በኒስ ያለው ኮንትራት ያበቃውን የ21 አመቱን ፈረንሳዊ ተከላካይ  ማላንግ ሳር ለማዘዋወር እየሰራ ይገኛል።ፍራንክ ላምፓርድ ለቀጣዩ አመት እየተሰናዳ ይገኛል።
(Star)





በርንመዝ ዌልሳዊውን የ23 አመት አማካይ ዳቪድ ብሩክስ ተገቢው ዋጋ ከቀረበለት ለመሸጥ ዝግጁ ነው።ተጨዋቹ በማን ዩናይትድ በጥብቅ እንደሚፈለግ ይታወሳል።
(Express)





ቶተንሃም የቀኝ መስመር ተከላካዩን ማት ዶሀርቲ ከዎልቨርሀምተን ዎንደረርስ ለማዘዋወር ከጫፍ ደርሷል።ዎልቭስ የ28 አመቱን አየርላንዳዊ ከመሸጥ £20ሚ. ነው የሚፈልገው።
(Independent)





ስፔናዊው አማካይ ቲዬጎ አልካንታራ በስተ መጨረሻ ከባየርን ሙኒክ ጋር ሊለያይ መሆኑ ተገልጿል።ባየርን ሙኒክ £30ሚ. የሚፈልግ ሲሆን ሊቨርፑል ደግሞ የተጨዋቹ ፈላጊ ነው።
(Express)





ያለፈውን አመት በውሰት ሊድስ ዩናይትድ ያሳለፈውን የ22 አመቱን ተከላካይ ቢን ኋይት ለማቆየት ብራይተን አጥብቆ እየሰራ ነው።ተጨዋቹ በሊቨርፑል ፣ በቼልሲ እና በማን ዩናይትድ ይፈለጋል።
(Sun)





ከፓሪሰን ዤርመን ጋር የተለያየው ኡራጓዊው አጥቂ ኤዲንሰን ካቫኒ ከዩቬንትስ የቀረበለትን የዝውውር ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።ምክንያቱ ደግሞ ለቀድሞው ክለቡ ናፖሊ ያለውን ታማኝነት ለማሳየት ነው።
(Mail)


No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...