አዘጋጅ - ኢብራሒም ሙሐመድ
አትሌቲኮ ማድሪዶች አሁንም የአርሰናሉ አጥቂ አሌክሳንደር ላካዜቲ ላይ ፈላጊ ክለብ ሆነዋል። እንደ ማርካ ዘገባ ከሆነ አትሌቲኮዎች ለአርሰናል ቶማስ ሌማርን አልያም አንጀል ኮሪያን ወይም ቪቶሎን በዝውውሩ ውስጥ በአማራጭ ለማቅረብ ፍላጎት አላቸው።
በዚህ ክረምት አያክስ አምስተርዳምን መልቀቁ እርግጥ የሆነው ጆኒ ቫንድቢክን ለማስፈረም ባርሴሎናዎች ፍላጎት አሳድረዋል።ነገር ግን ተጨዋቹ ወደ ስፔን ላሊጋ ከመዘዋወር ይልቅ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ማምራትን እንደሚፈልግ የስፔኑ Sport Media አስነብቧል።
ቤን ቺልዌል ወደ ቸልሲ የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ ከጫፍ ደርሷል።ቸልሲ እና ሌስተር በዝውውር ጉዳይ £50m የተስማሙ ሲሆን ቸልሲም ከተጨዋቹ ጋር በግል ተስማምቷል።የተጨዋቹ ዝውውር ዛሬ ምሽት ይፋ ሊደረግ እንደሚችል Sky Sport አስነብቧል።
ማንችስተር ሲቲዎች ሴኔጋላዊውን የናፖሊ ተከላካይ ካሊዱ ኩሊባሊን ለማስፈረም ለናፖሊ ከገንዘብ ጋር ተጨዋች ለማቅረብ ፍላጎት አሳይተዋል።እንደ ቶልክ ስፖርት ዘገባ ሲቲዎች በናፖሊ የሚፈለግውን ሩዲ ጋርሲያን ለመስጠት እና ተጨማሪ ብር ለመክፈል ፍቃደኛ ሆነዋል።
ወልቭሶች ለአርሰናሉ የመስመር ተመላላሽ ሚትላንድ ናይልስ ያቀረቡት £20m ጥያቄ ውድቅ ተደርጎባቸዋል።ወልቭሶች ተጨዋቹን ለማስፈረም ገፍተው ቢመጡም አርሰናሎች ግን ከተጨዋቹ የተሻለ ገንዘብ ስለሚፈልጉ ጥያቄውን ውድቅ አድርገውባቸዋል።
የተጨዋቾቻቸውን ውል በማራዘም የተጠመዱት ሌስተር ሲቲዎች ከቀናት በፊት የማዲሰንን ውል ሲያራዝሙ ዛሬ ከሰአት ደግሞ የዘንድሮ የፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ግብ አስቆጣሪውን የጂሚ ቫርዲን ውል ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።
ኤቨርተኖች ኮሎምቢያዊውን ሀሜስ ሮድሪጌዝን ለማስፈረም ከጫፍ እንደደረሱ ማርካ አስነብቧል።እንደ መረጃው ከሆነ ኤቨርተኖች ተጨዋቹን በውሰት ነው ማስፈረም ሚፈልጉት ነገር ግን ያማይሳካ ከሆነ ልጁን በቋሚ ለማስፈረም ይገደዳሉ።ተጨዋቹ በቱርኩ ክለብ ጋላታሳራይም ይፈለጋል።
ቶተንሀሞች አየርላንዳዊውን የወልቭስ የመስመር ተጨዋች የሆነውን ማት ዶኸርቲን ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው። ነገር ግን ወልቭሶች ተጨዋቹን ለቶተንሀም አሳልፈው ለመስጠት የሚትላንድ ናየልስን ዝውውር ማጠናቀቅ ብቻ እየጠበቁ ይገኛሉ።የዶኸርቲ ዝውውር መፈፀሙ አይቀሬ ነው።
ክሮሺያዊው ኢቫን ራኪቲች ከካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ለመልቀቅ ከጫፍ ደርሷል።እንደ AS ዘገባ ከሆነ ተጨዋቹ በቀጣይ ቀናት ወደ ቀድሞ ክለቡ ሲቪያ ለመመለስ ድርድር እንደሚጀምር ታውቋል።

No comments:
Post a Comment