አዘጋጅ - ኢብራሒም ሙሐመድ
ቸልሲዎች ተጨዋቾችን ከማስፈረማቸው በፊት ልጆችን ለመልቀቅ ፍላጎት አላቸው። ቸልሲዎች የመጀመሪያ ሽያጭ ለማድረግ የወሰኑት የግራ መስመር ተከላካዩን ኤመርሰን ፓልሜራስን ለመሸጥ ወስነዋል። ቸልሲዎች ለተጨዋቹ ለሚመጡ ጥያቄዎች £26m በታች ላለመስማት ወስነዋል።
የአንቾሎቲው ኤቨርተን ስማቸው ከተለያየ ተጨዋቾች ጋር እየተያያዘ ነው። አንቾሎቲ የመሀል ሜዳውን ለማጠናከር ፊታቸውን ወደ ታታሪው የዋትፎርድ አማካይ አብዱላዪ ዶኮሬ አዙረዋል።ዋትፎርዶች ከተጨዋቹ እስከ £35m ይፈልጋሉ።
አርሰናሎች አሁንም የቶማስ ፓርቲ ፈላጊ ሆነው ብቅ ብለዋል።በዚህ የክረምት የዝውውር መስኮት ልጁን እንደሚያስፈርሙት የተማመኑት መድፈኞቹ ባሳለፍነው ሳምንት ለአትሌቲኮ ማድሪድ ጥያቄ ማቅረባቸውን Sport አስነብቧል።እንደመረጃው ከሆነ አርሰናሎች ለ27 አመቱ ጋናዊ ኮከብ ማቲዩ ጉንዶዚንን እና ተጨማሪ £22m ቢያቀርቡም በአትሌቲኮ ውድቅ ተደርጎባቸዋል።
ሮማዎች በድጋሚ የክሪስ ስሞሊንግ ፈላጊ ሆነው ብቅ ብለዋል።የዘንድሮውን ሲዝን በሮማ ያሳለፈው ስሞሊንግ በተለያዩ የእንግሊዝ ክለቦች ቢፈለግም ተጨዋቹ ግን ወደ ጣሊያን መመለስን መርጧል። ሮማዎች ለስሞሊንግ £17m ለመክፈል ፍቃደኛ ቢሆኑም ዩናይትዶች ግን ከተጨዋቹ ከ£20m በታች እንደማይቀበሉ ነግረዋቸዋል።
ፒኤስጂዎች ካቫኒን ማጣታቸውን ተከትሎ በሱ ምትክ አጥቂዎችን ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው።እንደ Sport ዘገባ ከሆነ ፔዤዎች በኪዩማን እንደማይፈለግ የተነገረውን ሉዊስ ስዋሬዝን ወደ ፓርክ ደፕሪንስ ለመውሰድ ይፈልጋሉ።ተጨዋቹ ከፔዤ በተጨማሪ በልጅነት ክለቡ አያክስም ይፈለጋል።
ቫሌንሲያዎች የሪያል ማድሪዱን አጥቂ የቦርጃ ማዮራልን ዝውውር ለመጨረስ ከጫፍ ደርሰዋል። ያለፉትን ሁለት አመታት በውሰት በሌቫንቴ ያሳለፈውን አጥቂ ለማስፈረም ቫሌንሲያዎች ለሪያል ማድሪድ ከ£15-£18m ለመክፈል ፍቃደኛ ናቸው። ተጨዋቹ በቀጣይ ቀናት በይፋ ቫሌንሲያን እንደሚቀላቀል ሙንዶ ዲፖርቲቮ አረጋግጧል።
ማንችስተር ዩናይትዶች ሙሉ ለሙሉ ከጃደን ሳንቾ ዝውውር ራሳቸውን ሊያገሉ እንደሆነ M.E.N አስነብቧል። ዩናይትዶች በተደጋጋሚ ከልጁ ጋር ስማቸው ሲነሳ ቆይቷል። ነገር ግን ዩናይትዶች ከዶርትመንድ ባለስልጣኖች ቁርጥ ያለ የዝውውር ሂሳብ እንዲከፍሉ ተነግሯቸዋል ነገር ግን ዩናይትድ ዶርትመንድ የጠየቀውን £108m ለመክፈል ፍቃደኛ አይደለም። ይህን ተከትሎ እስከ ቀጣዩ ሲዝን እራሳቸውን ከዝውውሩ ለማውጣት ፈልገዋል።
ጁቬንቱሶች የፒኤስጂውን ሊአናርዶ ፓራዴዝን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ስካይ ስፖርት አስነብቧል።ተጨዋቹ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ክለቡን መልቀቅ ይፈልጋል።ይህን ተከትሎ ጁቬንቱሶች ልጁን ለማስፈረም ዝግጁ ሆነዋል።
ያልተሳካ አመት ከኤቨርተን ጋር ያሳለፈው ሞይስ ኪን የውሰት ውሉን በመጨረሱ ወደ ጁቬንቱስ ተመልሷል።ተጨዋቹም በፔርሎ ቡድን ውስጥ ቦታ እንደሌለው የተነገረው ሲሆን ወደ ሌላ ክለብ እንዲዘዋወር ፍቃድ ሰተውታል።ጁቬዎች ልጁን በውሰትም ሆነ በቋሚ ልጁን ለሚፈልግ ማንኛውም ክለብ ለድርድር ዝግጁ ናቸው።
No comments:
Post a Comment