አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ
አርሰናሎች አዲሱ የስፔናዊው ቲያጎ አልካንትራ ፈላጊ ሆነው ብቅ ብለዋል። ክለባችውን በማጠናከር ላይ የሚገኙት አርሰናሎች የ29 አመቱን ኮከብ ከባየርን ሙኒክ ለማስፈረም ሊቨርፑልን ለመፎካከር ፍላጎት አላቸው። አርሰናሎች አልካንትራን ለማምጣት ቶሬራን እና ኤልኔኒን ለሽያጭ አቅርበዋል።
ባሳላፍነው ክረምት ወደ ኢንተር ሚላን ያመራው ጣሊያናዊው አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ከኢንተር ጋር ሊለያይ ይችላል።ከክለቡ ሰዎች ጋር ብዙም ጥሩ ግንኙነት የሌለው ኮንቴ እለተ ማክሰኞ ከክለቡ ሰዎች ጋር ለመነጋገር ቀጠሮ ተይዞለታል።በተጨማሪም ኢንተሮች ኮንቴን አሰናብተው አሌግሪን ለማምጣት ፍላጎት አላቸው።
የቀድሞ የሊቨርፑል እና ኤሲሚላን ግብ ጠባቂ ፔፔ ሬና ዳግም ወደ ጣሊያን ሴሪያ ለመመለስ ከጫፍ ደርሷል። በዘንድሮ ሲዝን ለአስቶን ቪላ 12 ጨዋታዎችን ብቻ መጫወት የቻለው ሬና የኢንዛጊውን ላዚዮ በሁለት አመት ኮንትራት ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል። ዝውውሩም በቅርብ ቀናት ውስጥ ያጠናቅቃል ተብሏል።
ባሳለፍነው ሳምንት የባርሴሎና አሰልጣኝ ሆነው የተሾሙት ሮናልድ ኪዩማን ቡድኑን እንደ አዲስ ለመገንባት ተጨዋቾች እንዲለቁ እያሳወቁ ይገኛሉ።እንደ ማርካ ዘገባ ከሆነ ረጅም አመት ክለቡን ያገለገለውን ሉዊስ ሱዋሬዝ እና ኢቫን ራኪቲች ሌላ ክለብ እንዲፈልጉ በኩዩማን በይፋ እንደተነገራቸው አስነብቧል።
ቸልሲዎች በቀጣይ ሳምንት ሶስት ዝውውሮችን እንደሚያጠናቅቁ ተማምነዋል። እንደ ስካይ ስፖርት ዘገባ ቸልሲዎች በቅድሚያ የባየርን ሌቨርኩሰኑን ካይ ሀቨርትስን ዝውውር ለመጨረስ ከምንም ጊዜውም በላይ ተቃርበዋል።እንዲሁም የሌስተሩን ቤን ቺልዌልንም ዝውውር ለመጨረስ ከሌስተር ጋር ከስምምነት ሲደርሱ ሌላኛው ቲያጎ ሲልቫን በነፃ ማስፈረም ሲሆን የሱም ዝውውር የቀናት እድሜ ብቻ ነው የሚቀረው።
አስቶን ቪላዎች ኬራን ቲሪፒየርን ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለመመለስ እየሰሩ እንደሆነ ተነግሯል። ባሳለፍነው ሲዝን ቶተንሀምን ለቆ ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ ያቀናው ቲሪፒየር እንዳስበው ህይወት በስፔን አልሆነለትም። ይህን ተከትሎ ቪላዎች ልጁን ወደ እንግሊዝ ለመመለስ እየሰሩ ነው።
ጁቬንቱሶች አዲሱ የቶማስ ፓርቲ ፈላጊ ክለቦች ሆነው መተዋል። ለረዥም ጊዜ በአርሰናል ራዳር ውስጥ የቆየውን ፓርቲን ለማስፈረም ጁቬዎች አትሌቲኮ ማድሪድ የሚፈልገውን £50m ለመክፈል ፍቃደኛ ናቸው።
No comments:
Post a Comment