አዘጋጅ - ኢብራሒም ሙሐመድ
ጁቬንቱሶች አሮን ራምሴ ለሽያጭ አቅርበውታል። ባሳለፍነው ሲዝን ከአርሰናል በነፃ ጁቬንቱስን ቢቀላቀልም የተጠበቀውን ያክል ሳይሆን በዚ የዝውውር መስኮት ክለቡን እንዲለቅ ተነግሮታል።ተጨዋቹንም ለማስፈረም ለሚፈልግ ክለብ ጁቬዎች እስከ £30m ይፈልጋሉ።ተጨዋቹ የቀድሞ ክለቡ አርሰናል እንዲሁም የኦሌው ማንችስተር ዩናይትድ እንዲሁም የኑኖው እስፕሪንቶ ወልቭስ ይፈልጉታል።
የግራ መስመር ተከላካያቸውን ቤን ቺልዌልን ለቸልሲ አሳልፈው ለመስጠት የቀረቡት ሌስተር ሲቲዎች በሱ ምትክ ሌላ ተጨዋች ለማስፈረም ወደ ገበያ መውጣታቸውን ዴይሊ ሜይል አስነብበዋል። እንደ ዘገባው ከሆነ ሌስተሮች የአያክስ አምስተርዳሙን የግራ መስመር ተከላካይ ኒኮላስ ታግሊአፊኮን ነው ለማስፈረም ፍላጎት ያሳዩት። ቤን ቺልዌል በዚህ ሳምንት የቸልሲ ዝውውሩን ያጠናቅቃል።
ማንችስተር ዩናይትዶች ፊታቸውን ወደ ፈረንሳዊው ኮከብ ኒጎሎ ካንቴ አዙረዋል።እንደ ማንችስተር ከተማ M.E.N ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ ዩናይትዶች ሳይጠበቅ ለተጨዋቹ ይፋዊ ጥያቄ ለቸልሲ ለማቅረብ ዝግጁ ናቸው። ዩናይትዶች ከካንቴ በተጨማሪ በመሀል ሜዳ ላይ የሳውል ኒግዌዝ ፈላጊ ናቸው።
በዘንድሮ ሲዝን የተከላካይ ክፍሉ ሲተች የሰነበተው የላምፓርዱ ቸልሲ የመሀል ተከላካይ ለማስፈረም ገበያ ላይ ከወጡ ሰንበትበት ቢሉም እስካሁን ግን ተጨዋች አላስፈረሙም። ትናንት ማምሻውን ግን የፈረንሳዩ ታማኝ ምንጭ ሌኪፕ ቸልሲዎች የፒኤስጂውን ብራዚላዊ ተከላካይ ቲያጎ ሲልቫን ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው።ቸልሲዎች ከተጨዋቹ ወኪል ጋር በይፋ ንግግር ለመጀመር በዚህ ሳምንት እንደሚገናኙም ታውቋል። የተጨዋቹም ማረፊያ ቸልሲ መሆኑ እርግጥ እየሆነ መቷል።
ማንችስተር ሲቲ እና ናፖሊ በካሊዱ ኩሊባሊ ዝውውር ላይ ከስምምነት መድረሳቸውን ካልቺዮ መርካቶ አስነብቧል።እንደ መረጃው ከሆነ ሲቲዎች ናፖሊ ለተጨዋቹ የጠየቀውን ገንዘብ ለመክፈል ፍቃደኛ ሆነዋል። ተጨዋቹም በግል ከሲቲ ጋር ከስምምነት ደርሷል።ማንችስተር ሲቲዎች ተጨዋቹን ይሄ ወር ሳይጠናቀቅ በማስፈረም ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ሲመለሱ በቋሚነት ለማስጀመር ፍላጎት አላቸው።
ቶተንሀሞች በዚህ ሳምንት አንድ አጥቂ ወደ ክለባቸው እንደሚቀላቅሉ ተማምነዋል። ስሙ ይፋ ባይደረግም ጆዜ እና ዳኒ ሌቪ በዚህ ሳምንት አንድ አጥቂ እንደሚያመጡ እርግጠኛ መሆናቸውን ዘሰን ዛሬ ጠዋት አስነብቧል። መረጃው ተጨዋቾቹን በእርግጠኝነት ባይጠቅስም ግን የበርንማውዙ ካሉም ዊልሰን አልያም የናፖሊውን አርጋዚ ሚሊክን ከሁለት አንዱን ሊያስፈርሙ እንደሚችል ተነግሯል።
አዲሱ የጁቬንቱስ አሰልጣኝ አንድሪያ ፔርሎ ጎንዛሎ ሂግዌንን በመልቀቅ በሱ ምትክ አጥቂዎችን ለማስፈረም ይፈልጋል።እንደ ስካይ ስፖርት ዘገባ ከሆነ ፔርሎ ሁለት አጥቂዎችን ወደ ቱሪን ለማምጣት ይፈልጋል። አጥቂዎቹም የወልቭሱ ራዎል ሂሚኔዝ እና የሮማው ኤዲን ዤኮ መሆናቸው ታውቋል።ፒርሎ ከተሳካለት ሁለቱንም ወደ ቱሪን ማምጣት አልያም አንዳቸውን ማምጣት እንደሚፈልግ ታውቋል።
ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደጉት የማርሴሎ ቤልሳው ሊድስ ዩናይትዶች የተለያዩ ተጨዋቾችን ለማስፈረም ፍላጎት እያሳዩ ነው።እንደ ስካይ ጣልያን ዘገባ ከሆነ ቤልሳ ስፔናዊውን የቫሌንሲያ ኮከብ ሮድሪጎ ሞሬኖን ለማስፈረም ይፈልጋሉ።
No comments:
Post a Comment