Sunday, August 23, 2020

የዕለተ እሁድ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

ዛሬ ምሽት የ2019/20 አውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ጨዋታ በሊዝበን ከተማ በባየርን ሙኒክ እና ፓሪሰን ዤርመን መሐከል ይደረጋል።ተጋጣሚዎቹን በሰፊ የግብ ልዩነት እየረታ የመጣው ባየርን ሙኒክ የተሻለ ጨዋታውን የማሸነፍ ዕድል እንዳለው ተተንብዩዋል።ከባየርን ሙኒክ በኩል ሌቫንዶልስኪ እና ዴቪስ ከፓሪሰን ዤርመን ደግሞ ምባፔ እና ኔይማር ተጽዕኖ እንደሚፈጥሩ ይጠበቃል።ጨዋታው ምሽት አራት ሰዓት ይደረጋል።




ማን ዩናይትድ ብራዚላዊውን የግራ መስመር ተጨዋች አሌክስ ሳንድሮ ለማዘዋወር ያቀረበውን £27ሚ. ዩቬንትስ አልተቀበለም።የጣሊያኑ ክለብ ተጨማሪ £9ሚ. ይፈልጋል።
(Joe)





በስተመጨረሻ ቼልሲ የ21 አመቱን ጀርመናዊ የመስመር አጥቂ ካይ ሀቨርት ለማዘዋወር ከጫፍ ደርሷል።ቼልሲ ከተጨዋቹ ባለቤት ባየርን ሊቨርኩሰን ጋር ስምምነት ላይ የደረሰ ሲሆን በቅርቡም ይፋ እንደሚደረግ ይታወቃል።
(Guardian)





ማን ዩናይትድ ሴኔጋላዊውን የ29 አመት ተከላካይ ኻሊዱ ኩሊባሊ ለማዘዋወር ከስምምነት ላይ መድረሱን በርካታ የአውሮፓ ሚዲያዎች በመዘገብ ላይ ናቸው።
( Sports Illustrated)






አዲሱ የዩቬንትስ አሰልጣኝ አንድሪያ ፒርሎ አርጀንቲናዊውን አጥቂ ጎንዛሎ ሂጎይን እና ጀርመናዊውን አማካይ ሳሚ ኬድራ ከስኳዱ ውጪ አድርጓቸዋል።
(Mirror)





አርሰናል የሊሉን ብራዚላዊ ተከላካይ ጋብሬል ማጋልሄስ ለማዘዋወር የሚያደርገውን ጥረት ከግብ እንደሚያደርሰው ተማምኗል።የ22 አመቱ ተጨዋች በማን ዩናይትድም ይፈለጋል።
(Independent)






ማን ዩናይትድ እንግሊዛዊውን የመስመር አጥቂ ጄደን ሳንቾ ለማዘዋወር ከቦሩሲያ ዶርትመንድ ጋር ሲያደርገው የነበረውን ድርድር ማቋረጡ ተገልጿል።ቀያይ ሰይጣኖቹ የ20 አመቱን ተጨዋች ለማዘዋወር ከአመት በኋላ እንደሚሞክሩም ኤክስፕረስ አስነብቧል።
(Sunday Express)





አርሰናል ስፔናዊውን አማካይ ቲዬጎ አልካንታራ ለማዘዋወር ለባየርን ሙኒክ ጥያቄ አቅርቧል።የ29 አመቱ አማካይ በሊቨርፑልም እንደሚፈለግ ይታወቃል።
(Mail on Sunday)





ባርሴሎና በቀጣይ ሳምንት ሊዮኔል ሜሲን በተመለከተ ያለውን አቋም እንደሚያሳውቅ ይጠበቃል።የ34 አመቱ የስድስት ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊ ከብሉግራናዎቹ ጋር እንደሚለያይ በሰፊው እየተነገረ ይገኛል።
(Clarin, via Mirror Online)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...