✅የናፖሊው አወዛጋቢ ፕሬዝደንት አውራሊዮ ደ ላውረንቲስ ሴኔጋላዊው ተከላካይ ካሊዱ ኩሊባሊን የሚሸጡት £81ሚ. ከቀረበላቸው መሆኑን ተናግረዋል።
(Sky Italia, via Metro)
✅ኦሌ ጉናር ሶልሻየር የማን ዩናይትድ አመራሮች የጄደን ሳንቾን ዝውውር በጊዜ እንዲጨርሱለት ይፈልጋል።ቦሩሲያ ዶርትሙንድም ከሊዮን ሜንፊስ ዴፓይን ለማዘዋወር እየሰራ ነው ፥ የሳንቾን ቦታ ለመተካት።
(ESPN)
✅ብራዚላዊው አማካይ ፌሊፔ ኩቲንሆ በእንግሊዞቹ አርሰናል እና ቶተንሃም እየተፈለገ ነው።አርሰናል ለዝውውሩ £9ሚ. እና ማቲዮ ጊውንዶዚን ለባርሴሎና አቅርቧል።
(Independent)
✅ቼልሲ ድንቁን የ21 አመት የባየርን ሊቨርኩሰን የጨዋታ ቀማሪ ካይ ሀቨርት ዝውውር ለመጨረስ ከጫፍ ደርሷል።
(Teamtalk)
✅ባርሴሎና በዘንድሮው የዝውውር መስኮት መጨረስ ከሚፈልጋቸው ዝውውሮች መሀከል የማን ሲቲው የ19 አመት ስፔናዊ የመስመር ተከላካይ ኤሪክ ጋርሲያ ዋነኛው ነው።
(Goal.com)
✅ጋቦናዊው ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግን ቼልሲ ባለፈው የጥር ወር የዝውውር መስኮት ሊያዘዋውረው ከጫፍ ደርሶ በደሞዝ ባለ መስማማታቸው ላይሳካ ችሏል።
(Mailonline)
✅ሪያል ቤቲስ በውሰት አርሰናል የሚገኘውን ስፔናዊውን አማካይ ዳኒ ሴባዮስ ለማዘዋወር እየሞከረ ነው።ሴባዮስ ንብረትነቱ የሪያል ማድሪድ ነው።
(Onda Cero, via Sun)
✅ባርሴሎና እና የዴቪድ ቤካሙ ክለብ ኢንተር ሚያሚ ብራዚላዊውን ዊልያን ለማዘዋወር ፍላጎት አላቸው።
(Sky Sports)
✅ቶተንሃም ፈረንሳዊውን አማካይ ታንጉይ ንዶምቤሌ እንዲሸጥ በኢንተር ሚላን የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።
(PA, via the42)
መልካም ምሽት!
No comments:
Post a Comment