ሊቨርፑል ከሰላሳ አመት በኋላ ሻምፒዮን የሆነበትን ዋንጫ ትናንት ተረክቧል።ቀያዮቹ ትናንት በ37ተኛ ሳምንት የእንግሊዝ
ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቼልሲን ገጥመው 5ለ3 ረትተዋል።የሊቨርፑል ደጋፊዎች ከስቴዲየም ውጪ ተሰብስበው ደስታቸውን ገልጸዋል።
ሊቨርፑልን ከሶስት አስርት አመታት በኋላ የሊጉ ባለ ክብር ያደረጉት የርገን ክሎፕ ትናንት ዋንጫውን ከተረከቡ በኃላ "ይሄ
በሽታ ሲያልፍ ትልቅ ፓርቲ ከደጋፊዎቻችን ጋር ይኖረናል" ብለዋል።
አርሰናል ጋቦናዊውን የ31 አመት አጥቂ ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ በክለቡ ለማቆየት አዲስ ኮንትራት ሊያቀርብለት ነው።አዲሱ ኮንትራት ለተጨዋቹ በሳምንት £250,000 የሚያስገኝለትም ይሆናል።
(Telegraph - subscription required)
በሳዑዲ አረቢያ ከበርቴዎች ሊሸጥ እንደሆነ እየተነገረለት ያለው ኒውካስትል ዩናይትድ ሰርቢያዊውን የሪያል ማድሪድ አጥቂ ሉካ ዮቪች በውሰት ለመውሰድ ከጫፍ ደርሷል።
(Shields Gazette)
በቀጣዩ አመት ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እንደሚያድግ ያረጋገጠው ሊድስ ዩናይትድ አንጋፋውን ስዊድናዊ አጥቂ ዝላታን ኢብራሒሞቪች ለማዘዋወር እየጣረ ነው።
(Sun)
በቼልሲ ያለው ኮንትራት ያበቃው ብራዚላዊው የመስመር አጥቂ ዊልያን ወደ አርሰናል ለመዘዋወር ድርድር እያደረገ ይገኛል።
(ESPN Brasil's Bruno Vicari on Twitter - in Portuguese)
ከሻምፒዮኑ ሊቨርፑል ጋር ያለው ኮንትራት ያበቃው አዳም ላላና ወደ ቀድሞው ክለቡ ሳውዝሀምተን ሊመለስ መሆኑ ተገልጿል።
(Express)
No comments:
Post a Comment