Wednesday, May 6, 2020
የዕለተ ረቡዕ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች
በብሩኖ ፈርናንዴዝ ዙሪያ ስፖርቲንግ ሊዝበን እና ሳምፕዶሪያ ክስ ላይ ናቸው።የዚህ ምክንያት ደግሞ ሳምፕዶሪያ ከብሩኖ ፈርናንዴዝ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ መዘዋወር ጋር የገንዘብ ጥያቄ ስላለው ነው።ጥያቄውም ስፖርቲንግ ሊዝበን £4ሚ. ሊከፍለኝ ይገባል የሚል ነው።ፈርናንዴዝ 2017 ላይ ነበር ከሳምፕዶሪያ ወደ ስፖርቲንግ ሊዝበን የተዘዋወረው።የ25 አመቱ ፖርቱጋላዊ በአሁኑ ሰዓት በማን ዩናይትድ ድንቅ ጊዜን እያሳለፈ ይገኛል።
(Mirror)
ማንቸስተር ዩናይትድ ፖል ፖግባን ለጁቬንትስ የሚሸጥ ከሆነ በምትኩ አሮን ራምሴን ወደ ኦልድ ትራፎርድ ማምጣት ይሻል።
(Express)
ሪያል ቤትሶች በክረምት ከቸልሲ ጋር ኮንትራቱ የሚጠናቀቀውን ፔድሮን ለማግኘት የሚደረገውን ፉክክር ተቀላቅለዋል።ተጨዋቹ በኒውካስትል እና በሮማ በጥብቅ ቢፈለግም ሪያል ቤትሶች ነቢል ፈኪርን በመሸጥ በምትኩ ፔድሮን በነፃ በክረምት ለማግኘት ፍላጎት አላቸው።
ማንችስተር ሲቲዎች አይናቸውን ወደ 23 አመቱ የሪቨር ፕሌት ተከላካይ ሉካስ ማርቲኔዝ ኳርታ አዙረዋል።እንደ ካልቺዮ መርካቶ ዘገባ ሲቲዎች ለተጨዋቹ እስከ £20m ለመክፈል ፍቃደኛ ናቸው። ተጨዋቹ በሪያል ማድሪድ እና በኢንተር ሚላንም ይፈለጋል።
ማንችስተር ዩናይትድ በሼፍልድ በውሰት እየተጫወተ የሚገኘውን ግብ ጠባቂያቸውን መሸጥ እንደማይፈልጉ ይፋ አድርገዋል። ሆኖም ተጨዋቹን በቀጣይ አመት ለሼፍልድ ዩናይትድ አልያም ለሌላ የፕሪሚየር ሊግ ክለብ በውሰት ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን M.E.N አስነብቧል።
አርሰናሎች የፈረንሳዊው ነቢል ፈኪር አዲስ ፈላጊ ሆነው ብቅ ብለዋል።ባሳለፍነው አመት ክረምት ከሊዮን ሪያል ቤትስን የተቀላቀለው ፈኪር በክረምት ወደ ሌላ ክለብ ማምራት እንደሚፈልግ ማርካ አስነብቧል።ተጨዋቹ ከአርሰናል በተጨማሪ በኤሲ ሚላንም ይፈለጋል።
ሊቨርፑሎች እስከ £110m በማውጣት ሁለት ዝውውሮችን ለመጨረስ ፍላጎት አሳይተዋል።እንደ Le10 Sport ዘገባ ከሆነ ሊቨርፑሎች በክረምት ቪክተር ኦሲምሄን በ£60m እና ቦባክሪ ሶማሬን £50m ነው ለማስፈረም የሚፈልጉት።ተጨዋቾቹ በቸልሲ በዩናይትድ እና በኒውካስትልም ይፈለጋሉ።
በዚ ሳምንት ባየርን ሙኒክን ሊቀላቀል ከጫፍ ደርሷል የተባለው የአርቢ ላይብዢኩ ዳዮት ኦፓሚንካኖ በሌብዢክ አዲስ ኮንትራት ለመፈረም መስማማቱን ስካይ ስፖርት አስነብቧል። ተጨዋቹ በሌብዢክ እስከ 2021 ኮንትራት ያለው ሲሆን ሌብዢኮች የተጨዋቹን ኮንትራት እስከ 2022 ለማድረግ ከስምምነት መድረሳቸው ተሰምቷል።
በክረምት ዊሊያንን እና ፔድሮን በነፃ የሚያጡት ቸልሲዎች በነሱ ምትክ ሌላ ተጨማሪ ተጨዋች ለማስፈረም ወደ ገበያ ወተዋል።እንደ Spanish website Todofichajes ዘገባ ከሆነ ቸልሲዎች በማድሪድ የ12 ወራት ኮንትራት ብቻ የሚቀረውን ቫስኬዝን ለማስፈረም ነው የፈለጉት። ሪያል ማድሪዶች ከተጨዋቹ እስከ £17m ብቻ ነው የሚፈልጉት።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል
"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...

No comments:
Post a Comment