Friday, May 1, 2020

የዕለተ አርብ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                        አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ


የአርሰናሉ ኡራጋዊ አማካይ ሉካስ ቶሬራ በክረምት የዝውውር መስኮት በድጋሚ ወደ ጣሊያን ሴሪያ መመለስ እንደሚፈልግ ተሰምቷል። እንደ ካልቺዮ መርካቶ ዘገባ የልጁ የረጅም ጊዜ ፈላጊ ለሆነው ኤሲ ሚላን መልካም ሚባል ዜና ሆኗል። መረጃውም አያይዞ አርሰናሎች ተጨዋቹን እስከ £25m በመሸጥ ለቶማስ ፓርቲ ዝውውር ለመሸፈንም እቅድ አላቸው ብሏል።





በክረምት ኮንትራቱ ከቸልሲ ጋር የሚጠናቀቀው ፔድሮ በክረምት ወደ ኒውካስትል ሊያመራ እንደሚችል The Chronicle አስነብቧል። በሳውዲ ባለሀብት መጠቃለላቸው እርግጥ እየሆነ ለመጣው ኒውካስትል ለመጫወት ፍላጎት አለው ፔድሮም። ክለቡንም ይረከባሉ በሚባሉት ፖቸቲንሆም ቢሆን የዝውውር እቅድ ውስጥ እንዳለ መረጃው አስነብቧል።





ለማንችስተር ዩናይትዶች መልካም ዜና ሚሆን ነገር ትናንት ማምሻውን ቢልድ ከወደ ጀርመን አስነብቧል። ቦሩሲያ ዶርትመንዶች ሳንቾን በክረምት ለቀው ተስፈኛውን የባርሴሎና ኮከብ አንሱ ፋቲን ለማስፈረም እንቅስቃሴ መጀመራቸውን አስነብቧል።ባርሴሎናዎች ተጨዋቹን ለመልቀቅ ፍቃደኛ ባይሆኑም ዶርትመንዶች ግን ልጁን ለማስፈረም ንግግር ለመጀመር ዝግጁ ሆነዋል።





ባየርን ሙኒኮች የጋናዊውን አማካይ ቶማስ ፓርቲ ዝውውር በይፋ ተቀላቅለዋል። በአርሰናል በጥብቅ እየተፈለገ የሚገኘውን ፓርቲን ለማስፈረም ሙኒኮች ዝግጁ ሆነዋል። ተጨዋቹም በሙኒክ የጃቪ ማርቲኔዝ ተተኪ በማድረግ ለማምጣት ነው ፍላጎት ያላቸው።





ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ የእንግሊዛዊው የቦሩሲያ ዶርትመንድ ኮከብ ጃደን ሳንቾን ዝውውር መቀላቀላቸውን ስፖርት ቢልድ አስነብቧል። መረጃው እንደሚያሳየው ከሆነ ተጨዋቹ ወደ ማንችስተር የመሄድ ፍላጎት ቢኖረውም ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ  ግን ልጁን ለማስፈረም የሚደረገውን ፉክክር ተቀላቅለዋል።





ሊቨርፑሎች ከሴኔጋላዊው ተከላካይ ካሊዱ ኩሊባሊ ጋር ግንኙነት እንደጀመሩ ዴይሊ ሜይል አስነብቧል። በአውሮፓ ካሉ ትላልቅ ተከላካዮች አንዱ የሆነው ኩሊባሊ በክረምት ናፖሊን መልቀቁ አይቀሬ ሆኗል። ናፖሊዎች ከተጨዋቹ አሁን ላይ £60m ይፈልጋሉ።





በዚህ ክረምት ኮንትራቱ ከበርንማውዝ ጋር የሚጠናቀቀው ፍሬዘር አርሰናል ከማምራት ይልቅ ወደ ቶተንሀም መሄድ እንደሚፈልግ Football insaider አስነብቧል። መረጃው እንደሚያሳየው ከሆነ ተጨዋቹ ቻምፒየንስ ሊግ መጫወት ይፈልጋል። ይህንንም ተከትሎ ምርጫው ቶተንሀም ሆኗል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...