Wednesday, April 29, 2020

የዕለተ ሐሙስ ማለዳ ስፖርታዊ ዜናዎች

                 አዘጋጅ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ኒውካስትል ዩናይትድ ለአረብ ባለሀብቶች ሊሸጥ መሆኑን ተከትሎ አዲሶቹ ባለቤቶች ማውሩሲዮ ፖቼቲንሆን ሆና አሰልጣኝ አድርገው ለመሾም አቅደዋል።አርጀንቲናዊው አሰልጣኝ የስቲቭ ብሩስን ቦታ ተክቶ ሲቀጠር በአመት £19ሚ. ሊከፈለውም ቃል ተገብቶለታል።
(Sky Sports)






የባየርን ሙኒኩ አሰልጣኝ ሀኒስ ፌሌክ ከጀርመናዊው የማንቸስተር ሲቲ አጥቂ ለሮይ ሳኔ ጋር ለ30 ደቂቃ ያህል በስልክ ተነጋግሯል።ሳኔ ስሙ ከባቫሪያው ክለብ ጋር ለብዙ ጊዜያት ሲያያዝ ሰንብቷል።
(Bild, via Goal - in German)





ማንቸስተር ዩናይትድ ጄደን ሳንቾን ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ የሚያመጣው ከሆነ ታሪካዊውን  7 ቁጥር ማሊያ ሊሰጠው ለእንግሊዛዊው አጥቂ ቃል ገብቶለታል።
(Mirror)





ፈረንሳዊው አማካይ ታንጉይ ንዶምቤይሌ መጪው የእግር ኳስ ህይወቱ በቶተንሃም እንደሚሆን ተስፋ አድርጓል ፥ ባርሴሎናም የልጁ ፈላጊ ነው።
(Sky Sports)






የሮማው አሰልጣኝ ፓውሎ ፎንሴካ ስፔናዊውን የመስመር አጥቂ ፔድሮ ከቼልሲ ማዘዋወር ይፈልጋል።
(Corriere dello Sport - in Italian)






አርሰናል ፈረንሳዊውን አጥቂ ኦድሱኒ ኤዶዋርድ ማዘዋወር ከፈለገ £25ሚ. መክፈል እንዳለበት በክለቡ ሴልቲክ ተነግሮታል።አርቴታ የአጥቂ ስፍራውን በእጅጉ ማጠናከር ይፈልጋል።
(Express)






የናፖሊው ቤልጄሚያዊ አጥቂ ድረስ መርትንስ ወደ ለንደን መጓዝን እንደሚሻ ተነግሯል።ቼልሲ ደግሞ ማረፍያው እንደሚሆን ይጠበቃል።
(Mail)






ኤሲ ሚላን ቀጣዩ የዝውውር መስኮት ሲከፈት አንጋፋውን ግብ ጠባቂ ፔፔ ሬና ለመሸጥ አቅዷል።የ37 አመቱ ግብ ጠባቂ በአሁን ወቅት በውሰት አስቶን ቪላ ነው የሚገኘው።
(Calciomercato)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...