አዘጋጅ - ኢብራሒም ሙሐመድ
ማንችስተር ዩናይትዶች የ29 አመቱ ዌሳን ቤንያደር ፈላጊ ሆነው መተዋል።ተጨዋቹ በሞናኮ ድንቅ ጊዜ እያሳለፈ ይገኛል። ይሄን ተከትሎ ዩናይትዶች ተጨዋቹን ወደ ኦልትራፎርድ ለማምጣት ፍላጎት እንዳላቸው ሌኪፕ አስነብቧል። ሞናኮዎች ከሲቪያ በ£29m ነበር ያስፈረሙት። ተጨዋቹ በዘንድሮ የፈረንሳይ ሊግ1 በ26 ጨዋታ 18ጎሎችን እና 7 አሲስት ማድረግ ችሏል። ተጨዋቹ ከዩናይትድ በተጨማሪ በአርሰናል፣ በሊቨርፑል፣ ቶተንሀም ፣ ሪ.ማድሪድ ፣ አ.ማድሪድ እና ቫሌንሲያ ይፈለጋል።
የባየርን ሙኒኩ አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ ከጀርመናዊው የማንችስተር ሲቲ የመስመር ተጨዋች ሊውሬ ሳኔ ጋር በዝውውር ጉዳይ ለ30 ደቂቃ በስልክ እንዳወሩ Sport Bild አረጋግጫለው አለ።ተጨዋቹ ለረጅም ጊዜ በባየርን ሙኒክ ራዳር ውስጥ እንደሚገኝ ይታወቃል።
ሳውዛንብተኖች ለሞሀመድ ኢሊዮንሲ ለሚመጣላቸው የዝውውር ጥያቄ ለመስማት ዝግጁ ሆነዋል። ሳውዛንብተኖች ለ25 አመቱ የመስመር ተጨዋች £10m ይፈልጋሉ። ተጨዋቹን ለማስፈረም የቀድሞ ክለቡ ሴልቲክ እና ሪያል ሶሴዳድ ፍላጎት አሳይተዋል።
አርሰናሎች በክረምት ተከላካይ ለማስፈረም ወደ ገበያ እንደሚወጡ ተሰምቷል።አንደ ስፔኑ As ዘገባ ከሆነ አርለናሎች ፊታቸውን ወደ ሪያል ማድሪዱ ተከላካይ ኤደር ሚሊታኦ አድርገዋል። ተጨዋቹ በዚህ ሲዝን በማድሪድ የፈለገውን ያክል ጥሩ ጊዜ እያሳለፈ አይገኝም። ይህንን ተከትሎ ተጨዋቹ በክረምት ክለቡን ለመልቀቅ መወሰኑ ተሰምቷል ፥ ተጨዋቹ በማንችስተር ሲቲም ይፈለጋል።
አርሰናል ፣ ቸልሲ ፣ ኤቨርተን እና ሌስተር ሲቲ የሊሉን ተከላካይ ጋብርኤልን ማስፈረም እንደሚፈልጉ የፈረንሳዩ ሚዲያ Le10 Sport አስነብቧል።ኤቨርተኖች ሊሎች ከ22 አመቱ ተጨዋች የሚፈልጉትን £30m ለመክፈል ፍቃደኛ ሆነዋል።
አርሰናል እና ቶተንሀም በፒኤስጂ በጥብቅ የሚፈለገውን በሲቪያ በውሰት እየተጫወተ የሚገኘውን ንብረትነቱ የሪያል ማድሪድ የሆነው ሰርጂዮ ሪዮግሊዮንን ለማስፈረም የሚደረገውን ፉክክር ተቀላቅለዋል።አርሰናሎች በቀጣይ አመት የኬራን ቴርኒ ተጠባባቂ ለማድረግ ያቀዱ ሲሆን ቶተንሀሞች ደግሞ የዳኒ ሮዝ ተተኪ ለማድረግ ፍላጎት አላቸው።
ሁለቱ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ሳይታሰብ ሆላንዳዊው የአያክስ ተጨዋች ጆኒ ቫንድቢክ ፈላጊ ሆነው ብቅ ብለዋል።እንደ Le10 sport ዘገባ ከሆነ ሁለቱ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ኤቨርተን እና ኒውካስትል ናቸው።
እንደ ጣሊያናዊው ጋዜጠኛ ቪንሴንዞ ሞራቢቶ ዘገባ ከሆነ የቸልሲው አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ ከናፖሊው ቤልጄማዊ አጥቂ ድረስ መርተንስ ጋር በየቀኑ በስልክ እንደሚያወሩ አረጋግጫለው ብሏል። በክረምት ከኮንትራት ነፃ የሚሆነው መርተንስ በብዙ ክለቦች ቢፈለግም ማረፊያው ቸልሲ እንደሆነ እየተረጋገጠ መቷል።
No comments:
Post a Comment