አዘጋጅ - ኢብራሒም ሙሐመድ
ማንችስተር ዩናይትዶች የፌድሪኮ ቼዛ ፈላጊ ሆነው ብቅ ብለዋል። ይህን የመስመር ተጨዋች ለማስፈረም ከዩናይትድ በተጨማሪ ቸልሲም ይፈልጋል።እንደ ዴይሊ ስታር ዘገባ ከሆነ ፊዮሬንቲና ከተጨዋቹ እስከ £60m ይፈልጋል።ተጨዋቹ ወደ እንግሊዝ ከመሄድ ይልቅ በጣሊያን መቆየት እንደሚፈልግ ተሰምቷል።
አርሰናሎች ኦባምያንግን በኢምሬትስ ለማቆየት የነበራቸው ተስፋ እንደተሟጠጠ ዘሰን አስነብቧል። ይህንንም ተከትሎ አርሰናሎች የአሮን ራምሴ እጣ ፋንታ እንዳይገጥማቸው በክረምት ወደ ገበያ እንደሚያወጡት ታውቋል ፥ አርሰናሎች ከተጨዋቹ £30m ይፈልጋሉ።
ኤቨርተኖች አሁንም ሀሜስ ሮድሪጌዝን ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው።አንቾሎቲ ለተጨዋቹ የአራት አመት ኮንትራት አዘጋጅተውለታል።እንደ ስፔናዊው ጋዜጠኛ Nicolò Schira ከሆነ ኤቨርተኖች የሮድሪጌዝ ዝውውር ማይሳካላቸው ከሆነ ፕላን B ፊሊፔ ኩቲንሆን ይዘዋል።
ሊቨርፑሎች ከሊሉ ናይጄሪያዊ የ21 አመት አጥቂ ቪክተር ኦስሚሄን ጋር ግንኙነት ጀምረዋል። እንደ Le Foot Mercato ከሆነ ሊሎች ከተጨዋቹ £70m ይፈልጋሉ።ተጨዋቹ ከሊቨርፑል በተጨማሪ ቸልሲም ይፈልገዋል። ተጨዋቹ በዘንድሮ የሊል ቡድን ውስጥ በ38 ጨዋታ 18 ጎሎችን አስቆጥሯል።
በዚህ ክረምት ኮንትራቱ ከፒኤስጂ ጋር የሚጠናቀቀው ኤዲሰን ካቫኒ በክረምት ወደ ሴሪያ ለመሄድ ፍላጎት እንዳለው ጋዜጣ ዴሎ ስፖርት አስነብቧል።ይህንንም ተከትሎ የ33 አመቱ ፈላጊ ለሆነው ኢንተር ሚላን መልካም ሚባል አጋጣሚ ሆኖላቸዋል።በተጨማሪም ተጨዋቹ በአትሌቲኮ ማድሪድ እና በዩናይትድ ይፈለጋል።
ማንችስተር ዩናይትድ ፣ ሪ.ማድሪድ እና ጁቬንቱስ የአያክሱ አማካይ የጆኒ ቫንድቢክ ዋነኛ ፈላጊ ሆነዋል። የ23 አመቱ አማካይ በክረምት ከዩሀንክራይፋ አሬና ለመልቀቅ ፍላጎት አለው።አያክሶች ከተጨዋቹ እስከ £45m-£54m ይፈልጋሉ።ተጨዋቹ በክረምት ጁቬንቱስን አልያም ማድሪድን መቀላቀል ይፈልጋል።
ፒኤስጂዎች የጋናዊው የ26 አመት የአትሌቲኮ ማድሪድ ቶማስ ፓርቲ ፈላጊ ሆነው ብቅ ብለዋል። አንደ RMC Sport ዘገባ ከሆነ ፒኤስጂዎች ለተጨዋቹ ይፋዊ ጥያቄ ሊያቀርቡ ዝግጁ እንደሆኑ ተነግሩዋል።አትሌቲኮዎች ከፓርቲ ዝውውር £50m ይፈልጋሉ። ተጨዋቹ ከፒኤስጂ በተጨማሪ በአርሰናልም ይፈለጋል።
ባየርን ሙኒኮች በትላልቅ የአውሮፓ ክለቦች አይን ውስጥ የገባውን የአርቢ ሌብዚጉን ፈረንሳዊ ተከላካይ ዳዮት አምፔካኖን ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸውን የጀርመኑ ታማኝ ጋዜጣ ቢልድ ዛሬ ጠዋት አስነብቧል።
No comments:
Post a Comment