አዘጋጅ - ኢብራሒም ሙሐመድ
ቶተንሀም ፣ ኢንተር ሚላን እና ጁቬንቱስ የባርሴሎናውን ብራዚላዊ አማካይ አርቱር ሜሎ ፈላጊ ሆነዋል። እንደ ካታላን ራዲዮ ዘገባ ከሆነ ባርሴሎና ተጨዋቹን በክረምት መልቀቅ ብዙም ባይፈልጉም ትላልቅ ተጨዋቾችን ለማስፈረም ሲሉ ግን ከሚለቋቸው ተጨዋቾች ውስጥ አርቱር እንዳለ ተሰምቷል።
ፒኤስጂዎች በክረምት የሚያጡትን የግራ መስመር ተከላካይ ካልቪን ኮርዛዋን ለመተካት የተለያዩ ተጨዋቾች እየተመለከቱ ነው። እንደ ማርካ ዘገባ ከሆነ ፒኤስጂዎች በዘንድሮ ሲዝን ባለቤትነቱ የሪያል ማድሪድ ሆኖ በሲቪያ በውሰት እየተጫወተ የሚገኘውን ሰርጂዮ ሪዮግሊዮንን ማስፈረም ይፈልጋሉ። ተጨዋቹም ቢሆን ወደ ማድሪድ የመመለስ ፍላጎት የለውም።
ሶስቱ የፕሪሚየር ሊግ ክለብ የሆኑት አስቶንቪላ ፣ ክርስቲያል ፓላስ እና ኒውካስትል በሄላስ ቬሮና ዘንድሮ ኮንትራቱ የሚጠናቀቀውን የመስመር ተጨዋች ፋቢዮ ቦሪኒን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል።የ29 አመቱ ቦሪኒ በሴሪያው ክለቦች ቢፈለግም ወደ ፕሪሚየር ሊግ መሄድን ምርጫው እንዳደረገ ተሰምቷል።
ጁቬንቱሶች በክረምት ጆኒ ቫንድቢክን አልያም ፖል ፖግባን ማስፈረም እንደሚፈልጉ ጋዜጣ ዴሎ ስፖርት አስነብቧል።መረጃው እንደሚያሳየው ከሆነ ጁቬዎች የመጀመሪያ ምርጫቸው ፖግባ ሲሆን የሱ ዝውውር ማይሳካ ከሆነ የአያክሱን ቫንድቢክን ማስፈረም እንደሚፈልጉ ታውቋል።
ትናንት ከሊቨርፑል ጋር ንግግር ላይ ነው የተባለው ዊሊያን ዛሬ ደግሞ በድጋሚ ስሙ ከአርሰናል እና ቶተንሀም ጋር መነሳት ጀምሯል። እንደ ESPN Brazil journalist Jorge Nicola ዘገባ ከሆነ ተጨዋቹ ወደ ኢምሬትስ የማምራት ፍላጎት አለው።በቸልሲ ቅርብ ጓደኛው የነበረው ብራዚላዊው ዳቪድ ሊዊዝ ወደ ኢምሬትስ እንዲመጣ ትልቁን ስራ እየሰራ እንደሆነ ጋዜጠኛው አረጋግጫለው ብሏል።
ቸልሲዎች ካሜሮናዊውን የአያክስ ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናናን ለማስፈረም የነበራቸውን ፍላጎት ትተውታል።እንደ ኤክስፕረስ ስፖርት ዘገባ ከሆነ ኦናና ከአያክስ ከወጣ መጫወት የሚፈልገው በ2015 ወደ አያክስ ወደ ላከው ባርሴሎና ነው።ይህንንም ተከትሎ ቸልሲዎች ከተጨዋቹ ዝውውር እራሳቸውን አግለዋል።
በሳኡዲ ባለሀብቶች ስር ሊሆን የተቃረበው ኒውካስትል በክረምት ተጨዋቾችን ለማስፈረም ከአሁኑ እንቅስቃሴ ጀምረዋል።እንደ Footmercato ዘገባ ከሆነ ኒውካስትሎች ኩሊባሊን ከናፖሊ ካቫኒን ከአያክስ እንዲሁም ነቢል ፈኪርን ከሪያል ቤትስ እንደሆነ ተሰምቷል።
ኤሲ ሚላኖች የሪያል ማድሪዱን አጥቂ ሉካ ዮቪችን የረጅም ጊዜ የክለቡ አጥቂ ማድረግ ይፈልጋሉ።በዘንድሮ ሲዝን በዚዳን ስር የተጠበቀውን ያክል ያላገለገለው ጆቪች በክረምት ክለቡን መልቀቁ አይቀሬ ሆኗል። እንደ ማርካ ዘገባ ማድሪዶች በክረምት ምባፔን ፣ ማርቲኔዝን ወይም ሀላንድን ማስፈረም ስለ ሚፈልጉ ተጨዋቹን አይፈልጉትም።
No comments:
Post a Comment