Monday, April 27, 2020

የዕለተ ሰኞ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


በውሰት ባየርን ሙኒክ የሚገኘው የባርሴሎናው አማካይ ፌሊፔ ኩቲንሆ ፥ ወደ መርሲሳይድ ለመመለስ ሊቨርፑል በድጋሚ እንዲያስፈርመው  ቢጠይቅም ቀያዮቹ ግን ብራዚላዊውን የ27 አመት አማካይ እንደማይፈልጉት ነግረውታል።
(Mirror)





አርሰናል ከፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ ጋር የነበረውን የኮንትራት ማራዘም ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።ጋቦናዊው ኢንተርናሽናል በማንቸስተር ዩናይትድ ፣ ኢንተር ሚላን ፣ ባርሴሎና ፣ ሪያል ማድሪድ እና ቼልሲ ይፈለጋል።
(Mirror)





ስፔናዊው ግብ ጠባቂ ዴቪድ ዴሄያ በማንቸስተር ዩናይትድ 'በርካታ አመታትን' መቆየት እንደሚፈልግ ተናግሯል።ሆኖም በውሰት ሼፍልድ ዩናይትድ የሚገኘው ዴን ሄንደርሰን ወደ ኦልድ ትራፎርድ የሚመለስ ከሆነ ፥ ዴሄያ በቋሚነት ለመሰለፍ ፈተና ይጠብቀዋል።
(Mail)





የኔይማር የቀድሞው ወኪል ዋግነር ሪቤይሮ ብራዚላዊው የአሁኑ የዓለማችን ውድ ተጨዋች የ17 አመት ልጅ ሳለ ቼልሲን ለመቀላቀል ተቃርቦ እንደነበር ተናግሯል።
(Mail)




የቼልሲው አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ የናፖሊውን አጥቂ ድረስ መርቲንስ በግል አውርቶታል።በአመቱ መጨረሻም የ32 አመቱን ቤልጄሚያዊ በነጻ ስታንፎርድ ብሪጅ ለማምጣት ተስፋን ሰንቋል።
(Mail)





በኢንትራክት ፍራንክፈርት አመቱን በውሰት ያሳለፈው ኔዘርላንዳዊው የመስመር ተከላካይ ጄትሮ ዊልያምስ ወደ ኒውካስትል ዩናይትድ መመለስ እንደሚፈልግ ተናግሯል።በቋሚነት ውል እንዲሰጠው እንደሚሻል አክሏል።
(Goal)





ቼልሲ ካሜሮናዊውን ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናና ከአያክስ ለማዘዋወር ያለው ፍላጎት የሚሰምርለት አይመስልም።ምክንያቱ ደግሞ የ24 አመቱ ግብ ጠባቂ ወደ እናት ክለቡ ባርሴሎና መመለስን ስለሚፈልግ ነው።
(Express)






No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...