አዘጋጅ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
ሮናልዶ ለስኬታማነት እጅግ በጣም በመታተር የሚታወቅ ሲሆን ማክቶሚናይም ስነ ልቦናውን ከፍ ለማድረግ የእርሱን መንገድ መከተልን ነው የመረጠው።
የ23 አመቱ አማካይ በእግር ኳስ ውስጥ አዎንታዊ የሆነ ስነ ልቦናን ማዳበር ለስኬታማነት ቁልፉ ነገር መሆኑን የተናገረ ሲሆን የሮናልዶም ስኬታማነት ምስጢር ይህ መሆኑን ተናግሯል።
ከማንቸስተር ዩናይትድ አካዳሚ ያደገው ማክቶሚናይ ፥ ለመጀመሪያ ጊዜ በዋናው ቡድን የመሰለፍ ዕድልን ያገኘው በጆዜ ሞሪንሆ ስር የነበረ ሲሆን አሁን በኦሌ ጉናር ሶልሻየር ስር ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሚባሉ ተጨዋቾች ውስጥ ራሱን ማስገባት ችሏል።
No comments:
Post a Comment