አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
ፓሪሰን ዤርመን ፈረንሳዊውን ኢንተርናሽናል ፖል ፖግባ ከማንቸስተር ዩናይትድ ለማዘዋወር አቅዷል።ፔዤ ይህንን ዝውውር እውን ለማድረግ ከገንዘብ በተጨማሪ አንሄል ዲማሪያን ወደ ኦልድ ትራፎርድ ለመሸኘትም ነው ያለመው።ዲማሪያ 2015 ላይ በቲያትር ኦፍ ድሪምስ ያልተሳካ ጊዜን ማሳለፉ ይታወሳል።
(Mail)
ምንም እንኳን ስሙ በስፋት ከቀድሞው ክለቡ ማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ቢያያዝም ክርስቲያኖ ሮናልዶ ፥ በጁቬንትስ ቤት እስከ 2022 መቆየት ይፈልጋል።
(Sun)
የሪያል ማድሪዱ አወዛጋቢ ፕሬዝደንት ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ አሁንም ብራዚላዊውን ኮከብ ኔይማር ለማዘዋወር ፍላጎት እንዳላቸው ለኔይማር ወኪል ተናግሯል።ኔይማር ከሎስብላንኮዎቹ በተጨማሪ በቀድሞው ክለቡ ባርሴሎናም በጥብቅ እንደሚፈለግ ይታወቃል።
(Goal)
የቶተንሃሙ አለቃ ጆዜ ሞሪንሆ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ቶማስ ሙኒርን ከፓሪሰን ዤርመን ለማዘዋወር ይፈልጋሉ።ከወዲሁም ተጨዋቹን በግል አውርተውታል።
(Express)
ፓሪሰን ዤርመን የ21 አመቱን ፈረንሳዊ አጥቂ ኪልያን ምባፔ ለሪያል ማድሪድ ከመሸጥ ይልቅ 'አመቱን ሙሉ ተቀያሪ ወንበር ላይ ቢያስቀምጠው ይመርጣል' ሲል ሰን አስነብቧል።
(Sun)
ቦሩሲያ ዶርትመንድ እንግሊዛዊውን አጥቂ ጄደን ሳንቾ በሲግናል ኢዱና ፓርክ እንደሚያቆይ ተማምኗል።የ20 አመቱ ተስፈኛ ኮከብ ከእንግሊዝ ክለቦች ጋር በተለይ ደግሞ ከማንቸስተር ዩናይትድ ፥ ስሙ በስፋት እየተያያዘ ይገኛል።
(Teamtalk)
በቀጣዩ አመት ሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ የወጠነው አርሰናል ፥ የአትሌቲኮ ማድሪዱን ጋናዊ አማካይ ቶማስ ፓርቲ ለማዘዋወር እየሰራ ነው።
(Express)
No comments:
Post a Comment