አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ
ቸልሲ እና ጁቬንቱስ ተጨዋቾቻቸውን ለመቀያየር ፍላጎት እንዳላቸው ቱቶ ስፖርት አስነብቧል።እንደ መረጃው ከሆነ ጁቬዎች ከቸልሲ ኤመርሰንን በመውሰድ በምትኩ አሌክሳንድሮን ለመስጠት ነው ፍላጎት ያላቸው።
በዚህ አመት ኮንትራቱ የሚጠናቀቀው እና በክረምቱ ክለቡን በነፃ መልቀቅ ሚችለው ዊሊያን የብዙ ክለቦች ጥያቄ ቢቀርብለትም አሁን ላይ ምርጫውን ሊቨርፑል አድርጓል። ዴይሊ ሜይል እንዳስነበበው ከሆነ አሁን ላይ ሊቨርፑል እና ዊሊያን ንግግር ላይ ናቸው።ወደ ስምምነት እንደደረሱ እና ዊሊያን በቅርብ ቀን በይፋ የቀዮቹ ንብረት እንደሚሆንም መረጃው ይፋ አድርጓል።
ቶተንሀሞች ሀሪ ኬንን በክረምት ሚያጡት ከሆነ የሱን ምትክ ለማግኘት አይናቸውን ወደ ቱርኩ ክለብ ፊነርባቼ አጥቂ ቬዳት ሙሪኪ ያዞራሉ።እንደ Turkish newspaper Aksam ቶተንሀሞች ተጨዋቹን በጥርም ለማስፈረም ሞክረው እንዳልተሳካላቸው ዘግቧል። በዘንድሮ የፊነርባቼ ቆይታው የ25 አመቱ አጥቂ በ28 ጨዋታ 15ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።
በክረምቱ ከአርሰናል ለመልቀቅ የተቃረበው ኦባምያንግ የቸልሲ የዝውውር እቅድ ውስጥ እንዳለ ተሰምቷል። ላምፓርድ ላውታሮ አልያም ዋርነርን ማስፈረም ካልቻሉ ኦባምያንግን ከአርሰናል ለማስፈረም ፍላጎት አለው። ኦባምያንግ ከቸልሲ በተጨማሪ በማንችስተር ዩናይትድ እና ሪ.ማድሪድም ይፈለጋል።
በቅርቡ በሳውዲ ባለሀብቶች ሊጠቃለሉ ከጫፍ የደረሱት ኒውካስትሎች አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ንግግሮችን ሊጀምሩ እንደሆነ ዴይሊ ስታር አስነብቧል። እንደ መረጃው ከሆነ ኒውካስትሎች የመጀመሪያ ምርጫቸው ማውሪሲዮ ፖቸቲንሆ ሲሆን ከአሰልጣኙ ወኪሎች ጋር ንግግር ሊጀምሩ እንደሆነ ተሰምቷል። በተጨማሪም ኒውካስትሎች አሌግሪን በአማራጭ ይዘዋቸዋል።
አርሰናሎች በክረምቱ ሁለት ዝውውሮችን እንደሚያጠናቅቁ ተማምነዋል። ኤክስፕረስ ስፖርት እንዳስነበበው ከሆነ አርሰናሎች በክረምቱ የዝውውር መስኮት ገንዘቦችን ከማውጣት ይልቅ ተጨዋቾችን በነፃ ማስፈረም እና በውሰት ማስፈረምን ምርጫቸው አድርገዋል።ይህንንም ተከትሎ በዚህ ክረምት በበርንማውዝ ኮንትራቱ የሚጠናቀቀውን ፍሬዘርን በነፃ ዝውውር እንዲሁም ሉካ ዮቪችን ከማድሪድ በውሰት እንደሚያስፈርሙት ተማምነዋል።
ማን.ዩናይትድ እና ኒውካስትል በሬንሱ ኮከብ ማውኦሳ ላይ ተፋጠዋል።እንደ ሌኪፕ ዘገባ ከሆነ ተጨዋቹ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ሄዶ መጫወት ይፈልጋል።እንደ መረጃዎች ከሆነ ኒውካስትሎች በጥር የዝውውር መስኮት ከሬንስ ልጁን ለመውሰድ £7m አቅርበው ውድቅ ተደርጎባቸዋል ፥ አሁን ላይ ከዩናይትድ በላይ ልጁን ለመውሰድ ፍላጎት አላቸው።
ባርሴሎናዎች በቸልሲ ፣ በሊቨርፑል እና በዩናይትድ የሚፈለገውን ጣሊያናዊ አማካይ ሳንድሮ ቶናሊን ለማስፈረም ንግግር ሊጀምር ነው።እንደ Corrierre della Sera ዘገባ ባርሴሎናዎች ልጁን ለማግኘት ለቤርሺያ እስከ £52m መክፈል አለባቸው።
No comments:
Post a Comment