አዘጋጅ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
ብራዚላዊው ኮከብ ኔይማር ፥ ወደ ቀድሞ ክለቡ ባርሴሎና መመለስን የሚፈልግ ከሆነ አሁን ከሚያገኘው በአመት £26ሚ. ገደማ ሊያጣ እንደሚችል ካታላን ዘመሙ ሙንዶ ዲፖርቲቮ አስነብቧል።
(Mundo Deportivo - in Spanish)
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ብዙ ክለቦች የሚያስገቡት ገንዘብ መውረዱ እሙን ሲሆን ፓሪሰን ዤርመንም የዚህ አደጋ ተጠቂ ነው።ሆኖም የፈረንሳዩ ክለብ ኪልያን ምባፔን በክለቡ ለማቆየት ከፍተኛ ገንዘብ እያሰናዳ ነው።
(ESPN)
የአሜሪካው ክለብ ኢንተር ሚያሚ ባለቤት የሆነው ዴቪድ ቤካም ኮሎምቢያዊውን አጥቂ ሀሜስ ሮድሪጌዝ ለማዘዋወር ከሪያል ማድሪድ ጋር እየተነጋገረ ነው።
(Goal)
የሳዑዲ አረቢያ ባለ ሀብቶች የእንግሊዙን ኒውካስትል ዩናይትድ ለመግዛት እየተደራደሩ ይገኛሉ።ከበርቴዎቹ ይህ ዕቅዳቸው ከሰመረ ኤዲንሰን ካቫኒን ከፓሪሰን ዤርመን ለማዘዋወር ያቀዱ ሲሆን ማሲሚሊያኖ አሌግሪን አሊያም ማውሩሲዮ ፖቼቲንሆን ደግሞ በአሰልጣኝነት መሾም ይፈልጋሉ።
(ESPN)
አርሰናል ጋናዊውን ኢንተርናሽናል ቶማስ ፓርቴ ለማዘዋወር ከክለቡ አትሌቲኮ ማድሪድ ጋር እየተነጋገረ መሆኑን የ26 አመቱ አማካይ አባት ይፋ አድርገዋል።
(Mail)
ቶተንሃም ባለቤትነቱ የባርሴሎና ሆኖ በውሰት ሪያል ቤቲስ እየተጫወተ ያለውን ብራዚላዊውን የመስመር ተከላካይ ኤመርሰን ለማዘዋወር ይፈልጋል።
(Mundo Deportivo - in Spanish)
አብዛኛዎቹ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ተጨዋቾቻቸውን ወደ ልምምድ ሊመልሱ ነው።የሚመለሱበትም ቀን ከአስራ አምስት ቀናት በኋላ በፈረንጆቹ ሜይ 9 ይሆናል።
(Sun)
No comments:
Post a Comment