አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ
ኤቨርተኖች አንድ ዝውውር እንደሚያጠናቅቁ ተማምነዋል።የአንቾሎቲው ኤቨርተን ያለበትን የመሀል ተከላካይ ችግር ለመቅረፍ የሊሉን ብራዚላዊ ተከላካይ ጋብርኤል ማግላሀስን ለማስፈረም ተቃርቧል።እንደ ዘጋርድያን ዘገባ ከሆነ ኤቨርተኖች ለተጨዋቹ እስከ £30m ለመክፈል ዝግጁ ናቸው።
የፍራንክ ላምፓርዱ ቸልሲ በክረምቱ የመሀል ተከላካይ ለማስፈረም ፍላጎት አላው። ይህንንም ተከትሎ ቸልሲዎች ፊታቸውን ወደ ኤሲሚላኑ አምበል ወደ ሆነው አሊሲዮ ሮማኞሊ አዙረዋል።እንደ ካልቺዮ መርካቶ ዘገባ ተጨዋቹ ከቸልሲ በተጨማሪ በናፖሊም ይፈለጋል።
ቶተንሀሞች የፒኤስጂውን ቤልጄማዊውን የቀኝ መስመር ተከላካይ ቶማስ ሙንየርን ለማስፈረም ተስፋ አድርገዋል። የጆዜው ቶተንሀም ያለበትን የቀኝ መስመር ተከላካይ ችግር ለመቅረፍ ከአሁኑ ሙንየርን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምሯል።የተጨዋቹ ኮንትራት በዚህ አመት ነው የሚጠናቀቀው።
ሁለቱ የለንደን ክለቦች ዌስትሀም እና ክርስቲያል ፓላስ በቀድሞ የሰንደርላንድ ተጨዋች በሆነው ጆሽ ማጃ ዝውውር ላይ ተፋጠዋል።የ21 አመቱ ናይጄሪያዊው አጥቂ በ2019 የጥር የዝውውር መስኮት ነበር ወደ ፈረንሳዩ ክለብ ቦርዶ ያመራው ፥ ነገር ግን ተጨዋቹ በድጋሚ ወደ እንግሊዝ መመለስ ይፈልጋል።
ቤልጄማዊው ድሬስ መርተንስ የመውጫ በር ላይ ቆሟል።ቤልጄማዊው ከናፖሊ ጋር ኮንትራቱ ዘንድሮ የሚጠናቀቅ ሲሆን እስካሁን የረባ የኮንትራት ጥያቄ ከናፖሊ ያልቀረበለት መርተንስ ኮንትራቱ ሲጠናቀቅ ክለቡን ለመልቀቅ ዝግጁ ነው።ተጨዋቹ በፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ይፈለጋል።
ባርሴሎናዎች ከማንችስተር ሲቲ ጋር የተጨዋች ልውውጥ ለማድረግ ዝግጁ ናቸው። እንደ Sport ዘገባ ከሆነ ባርሴሎናዎች ሀሳባቸው የቀኝ መስመር ተከላካይ ቅይይር ለማድረግ ነው ዝግጁ የሆኑት። በጋርዲዮላ የመሰለፍ እድልን እያገኘ የማይገኘውን ካንሴሎን በመውሰድ ሴሚዶን ለሲቲ ለመስጠት ዝግጁ ሆነዋል።
ማንችስተር ሲቲዎች ኩን አጉዌሮን የሚተካላቸው አጥቂ ለማስፈረም በክረምት ወደ ገበያ ለመውጣት ዝግጁ ሆነዋል።እንደ ዘሰን ዘገባ ከሆነ ሲቲዎች እስከ £97m በማውጣት ላውታሮ ማርቲኔዝን ሊያስፈርሙ ይፈልጋሉ።ከሲቲ በተጨማሪ ልጁ በባርሴሎና እና ቸልሲ ይፈለጋል።
No comments:
Post a Comment