Sunday, April 12, 2020

የዕለተ ሰኞ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                           አዘጋጅ - ኢብራሒም ሙሐመድ



ባርሴሎናዎች ለረጅም ጊዜ ሲፈልጉት የነበረውን ብራዚላዊውን የቸልሲ የመስመር ተጨዋች ዊሊያንን አሁን ላይ እሱን ለማስፈረም ከሚደረገው ፉክክር እራሳቸውን አግለዋል።መረጃው እንደሚያመለክተው ባርሴሎናዎች በክረምት ከዊሊያን ይልቅ ፍላጎታቸው ኔይማር ወይም ማርቲኔዝ ነው።





ማንችስተር ዩናይትድ እና አርሰናል የአለም ዋንጫ አሸናፊውን ኮረንቲን ቶሊሶን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል። በሙኒክ የተጠበቀውን ያህል እየተንቀሳቀሰ የማይገኘው እና በዚህ ሲዝን ብዙ የመሰለፍ እድልን እያገኘ የማይገኘው ቶሊሶ ክለቡን ለመልቀቅ ዝግጁ ነው። ተጨዋቹ በአ.ማድሪድ ፣ በጁቬንቱስ እና ናፖሊም ይፈለጋል።





ሁለቱ የማንችስተር ከተማ ክለቦች በስዋንሲ ሲቲው ተከላካይ ሮዶን ላይ ፍላጎት አሳይተዋል። እንደ WalesOnline ዘገባ ከሆነ የ22 አመቱን ሁለገብ ተከላካይ ለማስፈረም ሁለቱም ክለቦች እድል አላቸው።ስዋንሲዎች ከተጨዋቹ እስከ £20m ማግኘት ይፈልጋሉ።





ሪያል ማድሪዶች አዲሱን ጋላክቲኮ ለመገንባት በዚህ የዝውውር መስኮት እና በቀጣዩ የዝውውር መስኮት ትላልቅ ተጨዋቾችን በማስፈረም እውን ለማድረግ ጀምረዋል።እንደ As ዘገባ ከሆነ ማድሪዶች በዚህ ክረምት ፖል ፖግባን እንዲሁም በቀጣዩ አመት የክረምት የዝውውር መስኮት ክሊያን ምባፔን ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው።





ሪያል ማድሪዶች ሀሪ ኬንን ለማስፈረም በልዋጭ መልክ ተጨዋቾችን ሊያቀርቡ እንደሆነ ኤክስፕረስ አስነብቧል። እንደ መረጃው ከሆነ ማድሪዶች ለቶተንሀም ሀሜስ ሮድሪጌዝን እና ጋሪዝ ቤልን በመስጠት ነው ሀሪ ኬንን መውሰድ የሚፈልጉት።





አርሰናል እና ማንችስተር ዩናይትድ የአትሌቲኮ ማድሪዱን አማካይ ቶማስ ፓርቲን ዝውውር እየመሩ ነው።እንደ ሚረር ዘገባ ከሆነ ተጨዋቹ በተለይ በትላልቆቹ የሴሪያ ክለቦች ኢንተር ሚላን ፣ ሮማ እና ናፖሊ እየተፈለገ ይገኛል።ይሄን ተከትሎ ዝውውሩን ለማሸነፍ የእንግሊዞቹ ክለቦች እየመሩ ይገኛሉ።





ናፖሊዎች በካሊዱ ኩሊባሊ ቆይታ ላይ ተስፋ ቆርጠዋል። እንደ Corriere Dello Sport ዘገባ ከሆነ ናፖሊዎች ተጨዋቹን ለሽያጭ አቅርበውታል ነገር ግን የመሸጫው ዋጋ እጅግ የወረደ እንደሆነ መረጃው ይፋ አድርጓል።ተጨዋቹ በትላልቅ የአውሮፓ ክለቦች ይፈለጋል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...