አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ
ቶተንሀሞች ፈረንሳዊውን ግብ ጠባቂያቸውን ሁጎ ሎሬስን በሌላ ለመተካት ወደ ዝውውር ገበያው ሊወጡ ነው።እንደ Sport ዘገባ ከሆነ ቶተንሀሞች አይናቸውን ካሜሮናዊው የአያክስ ግብ ጠባቂ የሆነው አንድሬ ኦናና ላይ ጥለዋል። አያክሶች ከተጨዋቹ ዝውውር እስከ £35m ይፈልጋሉ።
በክረምት ባርሴሎናን መልቀቁ እርግጥ የሆነው አርትሮ ቪዳል ከቻይና ሱፐር ሊግ የቀረበለትን የእናዘዋውርህ ጥያቄ ውድቅ አድርጓል። እንደ fox Sport ዘገባ ከሆነ ለተጨዋቹ ከሁለት የቻይና ክለብ ጥያቄ ቢቀርብለትም ቪዳል ግን ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ ከቀድሞ አሰልጣኙ ጋር አብሮ ለመስራት ኢንተር ሚላንን ምርጫው አድርጓል።
ዎልቭሶች የመስመር አጥቂያቸውን የዝውውር ሂሳብ ከፍ አድርገዋል።በ2018 ከሚዲልስቦሮ ዎልቭስን በ£18m የተቀላቀለው አዳማ ትራኡሬ አሁን ላይ የብዙ ክለቦችን ቀልብ እየሳበ ይገኛል። ይህንን ተከትሎ ትራኦሬን ፈልጎ ለሚመጣ ክለብ ሁሉ ዎልቭሶች ከ£80m በታች የዝውውር ጥያቄ እንደማይሰሙ ይፋ አድርገዋል።
ጁቬንቱሶች አይናቸውን ወደ ጣሊያናዊው የቸልሲ የግራ መስመር ተከላካይ ኤመርሰን ላይ ጥለዋል። በላምፓርድ ስር ብዙም የመሰለፍ እድልን እያገኘ የማይገኘውን ኤመርሰንን ጁቬንቱስ በማስፈረም የአሌክሳንድሮ ተተኪ ማድረግ ፈልጋሉ።ቸልሲዎች ከተጨዋቹ እስከ £30m ይፈልጋሉ።
አርሰናሎች የሞሮኮዋዊ አሽራፍ ሀኪሚ አዲስ ፈላጊ ሆነው መተዋል።በዘንድሮ ሲዝን ከሪያል ማድሪድ በውሰት ዶርትመንድን እያገለገለ የሚገኘው ሀኪሚ ኮንትራቱ በቀጣይ ሲዝን ያልቃል። ይህን ተከትሎ ማድሪዶች ተጨማሪ ኮንትራት ከመስጠት ይልቅ ልጁን ለመልቀቅ ይፈልጋሉ።
ማንችስተር ዩናይትድ እና ናፖሊ ኮሎምቢያዊውን ሀሜስ ሮድሪጌዝን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል። ሀሜስን በዚህ የክረምት ዝውውር መስኮት ማድሪዶች እስከ £46m ለሚያቀርብ ክለብ ተጨዋቹን አሳልፈው ለመስጠት ዝግጁ ናቸው።
የቱርኩ ቤሺክታሽ የቀድሞውን የማንችስተር ሲቲ ግብ ጠባቂ ጆ ሀርትን ማስፈረም ይፈልጋሉ።ቤሺክታሾች በክረምት ከሊቨርፑል በውሰት ያመጡትን ካሪየስን በሀርት ለመተካት ዝግጁ መሆናቸውን Fanatik, in Turkish አስነብቧል።
No comments:
Post a Comment