Thursday, April 9, 2020

የዕለተ ሐሙስ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

                     አዘጋጅ - ኢብራሒም ሙሐመድ


ብሩኖ ፈርናንዴዝ ከፈረመ በኋላ ዩናይትዶች ሌሎች አማካዮችን ለማስፈረም እየሰሩ ነው።እንደ M.E.N ዘገባ ከሆነ ዩናይትድ ሁለቱን አማካዮች ግሪሊሽ እና ማዲሰን ኢላማ አድርጓል።በተጨማሪም የአያክሱ ቫንድቢክ በሶልሻየር በጥብቅ ሚፈለግ ነው።ሌላኛው የዩናይትድ ኢላማ ቤሊንግሀም ሲሆን ዩናይትድ በጥብቅ እየሰራበት ያለ ተጨዋች ነው።






ባሳለፍነው የክረምት የዝውውር መስኮት ከአያክስ ጁቬንቱስን ከተቀላቀለ በኋላ በጁቬንቱስ የተጠበቀውን ያክል ያልተንቀሳቀሰው ሆላንዳዊው ተከላካይ ማቲያስ ዴላይት በክረምት ክለቡን እንደማይለቅ ተረጋግጧል። ባሳለፍነው ሳምንት ስሙ ከዩናይትድ በፖግባ ቅይይር ስሙ ቢነሳም ተጨዋቹ ግን ምርጫው አሁንም ጁቬንቱስ ነው።






የናፖሊው አጥቂ አርካዜክ ሚሊክ በክረምት ክለቡን ለመልቀቅ ዝግጁ እንደሆነ ለተጨዋቹ ቅርብ የሆኑ ሰዎች ይፋ አድርገዋል ተጨዋቹን ኤሲሚላን ለማስፈረም ፍላጎት የነበራቸው ቢሆንም አሁን ላይ ሻልክ04 ለተጨዋቹ £25m ለማቅረብ ዝግጁ ሆነዋል ነገር ግን ናፖሊዎች ከተጨዋቹ £35m ነው የሚፈልጉት።






ቦሩሲያ ዶርትመንድ ጃደን ሳንቾን በክረምት በመልቀቅ በምትኩ በብዙ ክለቦች አይን ውስጥ የወደቀውን የቫሌንሲያውን ተጨዋች ፌራን ቶሬስን ማስፈረም እንደሚፈልጉ ኢንዲፔንደንት ዘግቧል።ቫሌንሲያዎች የብዙ ክለብ አይን ውስጥ የወደቀውን ልጃቸውን ለሚፈልግ ክለብ £88m ማቅረብ እንዳለበት ይፋ እንዳረጉ የሚታወስ ነው።






ሊቨርፑሎች የሲቪያውን የ27 አመት ብራዚላዊ ተከላካይ ዲዬጎ ካርሎስን ለማስፈረም ከሌሎች ክለቦች ጋር ተፋጠዋል። ክሎፕ ብራዚላዊውን የቫንዳይክ አጣማሪ ማድረግ ይፈልጋሉ። ተጨዋቹ በዘንድሮ የሲቪያ ቡድን ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ ሲወስድ እሱ በተሰለፈባቸው 31ጨዋታ ሲቪያ 13 ጊዜ ግብ ሳይቆጠርበት ወጥቷል። ተጨዋቹ በባርሴሎና እና በሁለቱ የማድሪድ ከተማ ክለቦች ይፈለጋል።





ቸልሲ እና ማንችስተር ዩናይትድ ከኡራጋዊው የፒኤስጂ አጥቂ ኤዲንሰን ካቫኒ ዝውውር እራሳቸውን አውጥተዋል።ኮንትራቱ በዚህ አመት ሚጠናቀቀው ካቫኒ በዚህ አመት መጨረሻ ወደ ኡራጋይ ተመልሶ የሀገሩን ክለብ ፔናሮልን ሊቀላቀል  እንደሚችል የሀገሩ ሚዲያዎች ይፋ አድርገዋል።





ባየርን ሙኒኮች በክረምቱ የዝውውር መስኮት ሶስት ዝውውሮችን እንደሚያጠናቅቁ ተማምነዋል።እንደ ቢልድ ዘገባ ከሆነ ሙኒኮች የመሀል እና የፊት መስመር ተጨዋቾችን ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው። ይህንንም ተከትሎ ሙኒኮች ለሮይ ሳኔን ከማን.ሲቲ ቲሞ ዋርነርን ከአር.ቢ ሌብዢክ እንዲሁም ካይ ሀቨርትዝን ከባየርን ሌቨርኩሰን ነው ለማስፈረም ፍላጎት ያላቸው እና እንደሚያስፈርሙ የተማመኑት።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...