አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ
አርሰናል እና ቶተንሀም የቸልሲውን የ31 አመት የመስመር አጥቂ ዊሊያንን ለማስፈረም ተፋጠዋል።የተጨዋቹ ኮንትራት በዚህ አመት የሚጠናቀቅ ሲሆን ቸልሲ እስካሁን ኮንትራቱን አላራዘመለትም። ይህንን ተከትሎ እዛው ለንደን የሚገኙት ሁለቱ ክለቦች ተፋጠውበታል።
አርሰናሎች የበርንማውዙን የመስመር ተጨዋች የሪያን ፍሬዘርን ዝውውር እንደሚያጠናቅቁ ተማምነዋል። የተጨዋቹ ኮንትራት በዚህ አመት ሚጠናቀቅ ሲሆን አርሰናል ተጨዋቹን በነፃ ለማስፈረም ዝግጁ ነው ፥ ዝውውሩንም እንደሚያጠናቅቁ ተማምነዋል።
ጂቬንቱሶች ፖግባን ለማዘዋወር ሲሉ ተጨዋቾቻቸውን ወደ ዝውውር ገበያ አውጥተዋል። ጁቬዎች ሪያል ማድሪድን በመቅደም በክረምት ፖግባን ለማዘዋወር እየሰሩ ይገኛሉ። እንደ ጋዜጣ ዴሎ ስፖርት ዘገባ ከሆነ ጁቬዎች ዳግላስ ኮስታ ፣ ሚራለን ፒያኒች እንዲሁም ፈርናንዲኮ በርናንዴስኪን ነው ለዝውውር ገበያ ያወጡት ይላል መረጃው።
ሪያል ማድሪዶች በፒኤስጂ ኮንትራት ለማራዘም ፍቃደኛ ያልሆነውን ፈረንሳዊ ኮከብ ክሊያን ምባፔን በ2021 የክረምት የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ከአሁኑ እንቅስቃሴ ሊጀምሩ ነው።እንደ As ዘገባ ከሆነ ኮንትራቱ 2022 የሚጠናቀቀው ምባፔ በቀጣይ አመት የመሸጫ ዋጋው ወደ £132m ስለሚቀንስ ማድሪዶች ምባፔን አግባብተው ኮንትራት ሳይፈርም ለፒኤስጂ ቀጣይ አመት ወደ በርናባው ሊያመጡት ነው።
በዚህ አመት ኮንትራቱ የሚጠናቀቀው ቤልጄማዊው የቀኝ መስመር ተከላካይ ቶማስ ሙንየርን ለማስፈረም ክለቦች ከአሁኑ ከተጨዋቹ ወኪል ጋር ንግግር እንደጀመሩ ተሰምቷል።እንደ ጋዜጣ ዴሎ ስፖርት ዘገባ ማንችስተር ዩናይትድ ፣ ኢንተር ሚላን እና ቶተንሀም የተጨዋቹ ፈላጊ ናቸው።
የኢቫን ራኪቲች የባርሴሎና ቆይታ በዚህ ክረምት እንደሚያበቃ እርግጥ ሆኗል። እንደ Sport ዘገባ ከሆነ ኮንትራቱ 2021 የሚጠናቀቀው ራኪቲች በቂ የመሰለፍ እድል ወደ ሚያገኝበት ክለብ ለማምራት ዝግጁ ነው። ተጨዋቹ እዛው ስፔን በአትሌቲኮ ማድሪድ ይፈለጋል።በተጨማሪም የፈረንሳዩ ሀብታም ክለብ ፒኤስጂም የልጁ ፈላጊ ነው። በተጨማሪም የጣሊያኖቹ ክለቦች ጁቬንቱስ ፣ ኤሲሚላን እና ኢንተር ሚላን ልጁን ይፈልጉታል።
የመሀል ተከላካይ ማስፈረም የዩናይትድ ተቀዳሚ ምርጫቸው አይደለም። ነገር ግን ማቲያስ ዲላይት እና ኩሊባሊ የዩናይትድ የረጅም ጊዜ ተፈላጊ ናቸው።
No comments:
Post a Comment